Connect with us

የልደቱ አያሌው ፍርድ ቤት የፈቀደው የዋስ መብቱ ዛሬም አልተከበረም

የልደቱ አያሌው ፍርድ ቤት የፈቀደው የዋስ መብቱ ዛሬም አልተከበረም
Photo: Social Media

ህግና ስርዓት

የልደቱ አያሌው ፍርድ ቤት የፈቀደው የዋስ መብቱ ዛሬም አልተከበረም

የልደቱ አያሌው ፍርድ ቤት የፈቀደው የዋስ መብቱ ዛሬም አልተከበረም
~ ፖሊስ ያልተለቀቀው ሌላ ክስ ስላለበት ነው ብሏል፣
~ ፍርድቤቱ የፖሊስን ምክንያት አልተቀበለውም፣

ዛሬ ጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ ም ከጠዋቱ በ4 ሰአት ላይ አቶ ልደቱ በተሰጣቸው ተለዋጭ ቀጠሮ በምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወንጀል ችሎት ቀርበዋል።

እንደሚታወቀው በዚህ ችሎት እየታየ ያለው አቶ ልደቱ አንድ ህገ ወጥ ሽጉጥ ተገኝቶባቸዋል በሚል የተከሰሱበት ክስ ነው።

በዚህ ክስ ይሄው ችሎት ለአቶ ልደቱ የ100 ሺ ብር አሲዘው ውጭ ወጥተው እንዲከራከሩ ቢወስንም ፖሊስ አለቅም በማለቱ ተፈፃሚ ሳይሆን ቀርቷል።

በሌላ ችሎት ፖሊስ ይግባኝ ቢጠይቅም ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የ100 ሺ ብር ዋስትናውን አፅንቶ አቶ ልደቱ እንዲፈቱ ቢወስንም በድጋሚ ፖሊስ አለቅም ብሎ እስከዛሬ አስሮ ይዟቸዋል።

በባለፈው ቀጠሮ ችሎቱ የአቃቢ ህግ ምስክሮችን ካደመጠ በኋላ ሁለት ትዕዛዞችን ማስተላለፉ አይዘነጋም።

1ኛ. አቶ ልደቱን ፍርድ ቤት በወሰነው ውሳኔ መሠረት ለምን እንዳልተለቀቁ የቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ቀርቦ እንዲያስረዳ። ትእዛዙንም አቶ ልደቱን አጅቦ የመጣው ፖሊስ እንዲያደርስ

2ኛ. አቶ ልደቱን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በአስቸኳይ እንዲለቅ ነበር

ስለዚህ የዛሬው ቀጠሮም ለምን የቢሾፍቱ ፖሊስ አለቅም እንዳለ ቀርቦ ሃላፊው እንዲያስረዳ እና አቶ ልደቱን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን መልቀቁን ለማረጋገጥ ነበር።

በዚህ መሠረት ዛሬ በችሎት የቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር ታሪኩ ለገሰ ቀርበው አስረድተዋል።

ኮማንደሩም
– እኔ ለተቋሙ አዲስ ስለሆንኩ ጉዳዩን አላውቀውም፣
– ከመርማሪው እንደተረዳሁት ሌላ ህገ መንግስቱን በሃይል ለመናድ በመሞከር በሚል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክስ ስላላቸው ነው ያልተለቀቁት ብሎኛል።
ስለዚህ ከበላይ ጋር በጉዳዩ ላይ ተነጋግሬ እንድመጣ ሌላ ቀጠሮ ይሰጠኝ በሚል ችሎቱን ጠይቋል።

ችሎቱም ከአንድም ሁለት ግዜ ፍርድ ቤት ያዘዘውን ትዕዛዝ አለመቀበል ተገቢነት የሌለው ድርጊት ነው። አዲስም ብትሆንም ፍርድ ቤት ያዘዘውን ትዕዛዝ ከማንም ጋር መምከር ሳያስፈልግ መልቀቅ ግዴታህ ነው።

ስለሌላው ክስ ይሄ ችሎት አይመለከተውም። በዚህ መዝገብ ትዕዛዝ ሰጥተናል። ስለዚህ ከፈለጋችሁ በዚያኛው ክስ የምትፈልጉትን ጥያቄ ማቅረብ ትችላላችሁ እንጂ የዚህን ችሎት ውሳኔ ማክበር አለባችሁ በማለት

1ኛ ኮማንደሩ በአስቸኳይ እንዲለቁት ትዕዛዙን የማይፈፅሙ ከሆነ ችሎቱ በሳቸው ላይ እርምጃ እንደሚወስድ፣

2ኛ አቶ ልደቱን እንዲለቅ ታዞ የነበረው የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ለምን ትእዛዝ እንዳላከበረ ቀርቦ እንዲያስረዳ በሚል ውሳኔ አስተላልፏል።(አዳነ ታደሰ ~ የኢዴፓ ሊቀመንበር)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top