Connect with us

ልደቱ አያሌው አዲስ ክስ ቀረበባቸው

ልደቱ አያሌው አዲስ ክስ ቀረበባቸው
Photo: Social media

ህግና ስርዓት

ልደቱ አያሌው አዲስ ክስ ቀረበባቸው

ልደቱ አያሌው አዲስ  ክስ ቀረበባቸው

አቶ ልደቱ አያሌው ላይ ከህገ መንግስት ውጪ ህገመንግስቱን በማፍረስ የሽግግር መንግስት መመስረቻ ሰነድ በማዘጋጀት በሚል ሌላ ክስ ቀረበባቸው፡፡

ክሱን ያቀረበው የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሲሆን÷ ክሱም በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምስራቅ ተዘዋዋሪ ምድብ ችሎት ነው፡፡ ችሎቱም የእምነት ክህደት ቃላቸውን ለመመልከት ለጥቅምት 5 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ 

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዛሬው ዕለት በአዳማ ከተማ የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከዚህ ቀደም ክስ በተመሰረተባቸው በህገወጥ የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት ላይ ምስክር ለመስማት ለጥቅምት 3 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል ሲል ፋና ዘግቧል፡፡

አቶ ልደቱ አያሌው ለሶስተኛ ጊዜ በዋስ በውጭ ሆነው እንዲከራከሩ ፍርድ ቤት የሰጠውን ትዕዛዝ ሳይፈጽም አስሮ በማቆየት የተለያዩ ክሶችን ሲያቀርብ ይህ ለሶስተኛ ጊዜ ነው፡፡

አቶ ልደቱ በትላንትናው ዕለት ችሎት ቀርበዋል። የትላንቱ ቀጠሮ በምስራቅ ሸዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት  የተጠረጠሩበት ወንጀል ያስከስሳል አያስከስስም የሚለውን ለመወሰን ነበር።

ችሎቱም ያስከስሳል ስለዚህ ለመጪው ማክሰኞ አቃቢ ህግ ምስክሮች አቅርቦ እንዲያስረዳ ተወስኗል። አቶ ልደቱም  “እስከ አሁን ከአንድም ሁለት ሶስቴ ፍርድ ቤቱ በኔ ላይ ውሳኔ ሰጠቷል። ነገር ግን ፖሊስ አለቅም ብሏል። ይሄ የሚያሳየው የታሰርኩት በፖለቲካ አስተሳሰቤ መሆኑን ነው። የሚፈለገው የኔን ድምፅ ማፈን ነው። ፍርድ ቤት፣ ዳኛ እና የፍትህ ስርአት ካልተከበረ አገር አለኝ ማለት አልችልም።

እኔ ፍርድ ቤት ነፃ አድርጎኝ ለ5 ደቂቃ የፍርድ ቤት ውሳኔ ተፈፃሚ ሆኖ ሌላ መጥሪያ ተሰጥቶኝ ብታሰር ደስ ይለኝ ነበር። ነገር ግን ፍርድ ቤት ቀጠሮ መሀል ችሎት የሚወስነው ውሳኔ ምን እንደሆነ ይጠበቅ እና ሌላ የክስ ቻርጅ እየተዘጋጀ በፍትህ ስርአቱ ነው መቀለድ የተያዘው። ስለዚህ ለችሎቱ ክብር እና ለተቋማችሁ ይህን ቀልድ አስቁሙልኝ” በማለት ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል ።

ፍርድ ቤቱም ፖሊስ ለምን አለቅም እንዳለ መርምረው ዛሬ ውሳኔ እንደሚሰጡ እና ጠበቆች ውሳኔውን መጥተው እንዲሰሙ ትእዛዝ ስለመስጠቱ አቶ አዳነ ታደሰ የኢዴፓ ሊቀመንበር በፌስ ቡክ ገጻቸው ካሰፈሩት ሐተታ መረዳት ተችሏል፡፡

 

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top