Connect with us

ልደቱን ፖሊስ አለቅም ማለቱ ተሰማ

ልደቱን ፖሊስ አለቅም ማለቱ ተሰማ
በድሬቲዩብ ሪፖርተር

ህግና ስርዓት

ልደቱን ፖሊስ አለቅም ማለቱ ተሰማ

የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተዘዋዋሪ ችሎት በዛሬው ዕለት፣ መስከረም 26 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት የዋስትና እግድን በተመለከተ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ይዞ የነበረ ሲሆን፣ የአቶ ልደቱ የዋስትና ጥያቄ እግድ አይገባውም፣ ዋስትና ሊፈቀድላቸው ይገባል የሚለውን የምስራቅ ሸዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወሰነውን በመቶ ሺህ ብር ዋስትና እንዲለቀቁ የሚለውን ውሳኔ አፅንቶ እንዲፈቱም ትዕዛዝ አስተላልፏል።

ይኸም ሆኖ ፖሊስ የፍ/ቤት ትእዛዝ አክብሮ አቶ ልደቱን አለመልቀቁን አቶ አዳነ ታደሰ የኢዴፓ ሊቀመንበር አረጋግጠዋል።

በተመሳሳይ ሁኔታ ከዚህ ቀደም አቶ ልደቱ ጉዳያቸውን ውጭ ሆነው እንዲከራከሩና፣ የዋስ መብታቸው እንዲከበር የምስራቅ ሸዋ ፍርድ ቤት ውሳኔ አሳልፎ የነበረ ሲሆን የቢሾፍቱ ፖሊስ በበኩሉ አቶ ልደቱ “በአደራ ነው” ያሉት በማለት አልለቅም ማለቱ ይታወሳል።

ይህንንም ጉዳይ ዛሬ በዋለው ችሎት ላይ አቶ ልደቱ ስጋታቸውን መግለፃቸውን አቶ አዳነ ይናገራሉ።

“ከዚህ በፊት የነበረውን ሁኔታ በመጥቀስ ፖሊስ አልለቅም ሊል ይችላል፤ ስለዚህ ፍርድ ቤቱ ከዚሁ በነፃ ያሰናብተኝ የሚል ጥያቄ አንስተው ፍርድ ቤቱ ግን ለፖሊስ በአስቸኳይ ትዕዛዝ የሰጠ ሲሆን፤ የ100 ሺህ ብር ዋስትናውን ለወሰነው ለምስራቅ ሸዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ትዕዛዙ እንዲደርስ በሚል ወስኗል” ብለዋል አቶ አዳነ።

ከዚህ ቀደም የምስራቅ ሸዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቶ ልደቱ በመቶ ሺህ ብር ዋስ ወጥተው ጉዳያቸውን ውጭ ሆነው እንዲከላከሉ በሚል ለመስከረም 20፣ 2013 ዓ.ም ውሳኔ አስተላልፎ ቀጠሮ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር።(ቢቢሲ እና አቶ አዳነ)

 

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top