“በጦርነት ላይ ብንሆንም ሁላችንም አንድ ነን…”
(ታምሩ ገዳ)
ለአላማችን ታላቅ ስጋት በሆነው በኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ረዳታቸው የሆኑት ሆፕ ሂክስ ተጠቅተው፣ እርሳቸውም ሆኑ ባለቤታቸው በወረርሽኙ እንደተጠቁ የገለጹት፣ በሜሪላንድ በሚገኘው በወተደራዊው ዎልተርድ ሪድ ሆስፒታል ውስጥ የሚገኙት የአሜሪካው ፕ/ት ዶናል ትራምፕ እንደ ዋሽንግተን ፖስት ዘገባ ” የኮሮና ምልክቶች የሆኑት አንስተኛ ትኩሳት፣መጠነኛ ጉንፋን እና የአፍንጫ መጨናነቅ ተከስቶባቸዋል” ይላል።
አንድ የዋይት ሀውስ ባለስልጣን በበኩላቸው “ፕ/ት ትራምፕ ከእድሜሜያቸው መግፋት ፣ከሰውነታቸው ክብደት እና ሌሎች ተዛማጅ ምክንያቶች ጋር በተያያዘ ለጥንቃቄ ሲባል በሆስፒታል እንዲቆዩ ተደርጓል” ብለዋል።
የ 74 አመቱ ፕ/ት ትራምፕን አና የ50 አመቷ ቀዳማዊት እመቤት ሚላኒ ትራምፕ የኮረና ቫይረስ ተጠቂ መሆንን ተከትሎ በአላማችን ላይ ከእስራኤል ጠ/ሚ/ር ናቲናኒያሁ አንስቶ የእንግሊዙ ጆንሰን፣፣የግብጹ አልሲሲ፣፣የሰሜን ኮሪያው ኪም ጆንግ ኡን፣ የቱርክ ኢርዲጋን ፣የሩሲያው ፑቲን …ወዘታ የመልካም ምኞት አስተያየቶችን አስተላልፈዋል።
ለትራምፕ ከረር ያለ መልእክት ከላኩት መካከል የፈረንሳይ መንግስት ቃል አቀባይ ገብሬል እታል” ቶሎ እንዲያገግሙ እንመኛለን፣ እግረመንገዳችንን ይህ ቫይረስ በጥርጣሬ አለም የሚገኙ እና አደገኛነቱን የሚክዱትን ጭምር እንደማይምራቸው አስተምሮናል” ብለዋል።
የቀድሞው የፖላንድ የውጪ ጉዳይ ሚኒስተር እና የአውሮፓ ህብረት የፓርላማ አባሉ ሲኪሮስኪይ ” የተከበሩ ፕሬዜዳንት የእቃ ማጠቢያ ብሊችን (bleach)እንደማይጠቀሙ እገምታለሁ”በማለት ትራምፕ ቀደም ሲል “ብሊችን መጠቀም ፈውስ ነው” ያሉበትን የተሳሳተ አስተያየትን አውስተዋል።
የቻይና የውጪ ጉዳይ ሚኒስተር ለ ፕ/ት ትራምፕ እና ለባለቤታቸው ቶሎ የመፈወስን ምኞቱን የገለጸ ሲሆን የቻይናው ኮሚኒስት ፓርቲ ጋዜጣ ግሎባል ታይምስ ዋና አዘጋጅ ዚጂን ” ፕ/ት ትራምፕ እና ቀዳማዊት እመቤት የኮሮና ቫይረስን በማጣጣላቸው ዋጋ አስከፈላቸው”ስል በትዊተር ገጹ ላይ አስፍሯል።
በአሜሪካ፣የጆርጂያ ግዛት የሪፖብሊካን ፓርቲ ሴንተር የሆኑት ኬሊይ ሎፍለር”ቻይና ይህንን ቫይረስን ለፕሬዜዳንታችን ሰጥታለች፣ ቤጂንግ ከተጠያቂነት አታመልጥም”ሲሉ ትዊተር ገጻቸው ላይ ቁጣቸውን ገልጸዋል ።
የቀድሞ የአሜሪካ ፕ/ት፣ ትራምፕ በብዙ መድረኮች ላይ በጽኑ የሚወርፏቸው ፕ/ት ባራክ ኦባማ “ምንም እንኳን በታላቅ የፖለቲካዊ ፍልሚያ ውስጥ ብንሆንም፣ያንን እንደ ዋና አቋም ብንወስደውም፣ በዚህ አጋጣሚ ለአሜሪካ ፕ/ት እና ለቀዳማዊት እመቤት ለሌሎችም ወገኖቻችን እኔ እና ባላቤቴ ሚሼል በፍጥነት እንዲያገግሙ እንሻለን። እኛ ሁላችን የሰው ልጆች ነን፣ አሜሪካኖች ነን፣ ሁሉም ሰው ጤናማ እንዲሆን እንመኛለን” በለዋል።