Connect with us

አዲሱ የኦሮሞ እና የአማራ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስምምነት

አዲሱ የኦሮሞ እና የአማራ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስምምነት
Photo: Social Media

ባህልና ታሪክ

አዲሱ የኦሮሞ እና የአማራ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስምምነት

አዲሱ የኦሮሞ እና የአማራ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስምምነት

ገዥውን ፓርቲ ብልፅግና ጨምሮ 11 የኦሮሞ እና የአማራ የፖለቲካ ፓርቲዎች በዛሬው ዕለት ተስማምተው የተፈራረሙባቸው 10 ነጥቦች:-

1. የሀገራችንን የፖለቲካ ችግሮችን ለመፍታት ሁሉን አካታች የሆነ ቀጣይ ሀገራዊ ውይይትና ድርድር ማካሄድ፤

2. ጥርጣሬ፣ መከፋፈል፣ እርስ በርስ መቃረን፣ አንዱ የሌላውን ስም ከማጥፋት እንዲሁም ሕዝብ ለሕዝብ ከሚያጋጩና ከሚያቃርኑ ድርጊቶች መቆጠብ፣

3. ሀገራዊ የህዝብ ቆጠራ ተአማኒነትና ተቀባይነት ባለው አሠራር በማካሄድ የሁሉም የሀገሪቱ ብሔር ብሐረሰቦች የሕዝብ ብዛት በአግባቡ ተቆጥሮ እንዲታወቅ ማድረግ፤ በትክክል እንዲቆጠር፣ የከዚህ በፊት ግድፈቶች የሚያርምና የማይደገምበት መሆኑን ማረጋገጥ፤

4. በሀገራችን ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን መገንባት፣ የግልና የቡድን መብቶችን ማስከበርና በየጊዜውና በየደረጃው ነጻና ፍትሐዊ ምርጫን ማካሄድ፣

5. በኢትዮጵያ የታሪክ አቀራረብ የታሪክ አንጓዎችን ተከትሎ ከሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች በተወጣጡ የታሪክ ምሁራን የሀገሪቱን ህዝቦች ግንኙነትና ታሪክ ጥናት እንዲካሄድ፤ የብሔረሰቦች ጥናት ተቋም እንዲቋቋም፣

6. በኦሮሞና አማራ ክልሎች የሚኖሩ የሁሉም ህዝቦች አባላት ደህንነትና መብቶች እንዲከበሩ፤

7. በሀገራችን የሁሉም አካባቢዎች ሰላምና ፀጥታ፣ ህግና ፍትህ ማስፈን፤ ከየቦታው ያለአግባብ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀያቸውና ኑሯቸው እንዲመለሱ እንዲደረግ፤

8. ሀገሪቱ የምትተዳረርበት ሕገ መንግሥት ሁሉን አሳታፊ በሆነ መንገድ እንዲሻሻል ማድረግ

9. በሀገሪቱ ዘላቂና ፍትሀዊ የኢኮኖሚ ልማት ማጎልበት፤ የህዝቦቻችንን ፍትሀዊ የኢኮኖሚና የሀብት ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፤

10. የተለያዩ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቶችንና ትብብሮችን የሚያጠናክሩ ዝግጅቶችን በጋራ ማዘጋጀት ናቸው።

(EBC)

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top