Connect with us

ቻይና አማርኛ ቋንቋን በመጀመሪያ ዲግሪ ልታስተምር ነው!

ቻይና አማርኛ ቋንቋን በመጀመሪያ ዲግሪ ልታስተምር ነው!
Photo: Social Media

ማህበራዊ

ቻይና አማርኛ ቋንቋን በመጀመሪያ ዲግሪ ልታስተምር ነው!

በቻይና ለመጀመሪያ ጊዜ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በዲግሪ ደረጃ ሊሰጥ ነው

በቻይና የቤጂንግ የውጭ ጥናቶች ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በመጀመሪያ ዲግሪ ደረጃ መስጠት ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ።

የዩኒቨርሲቲው የአማርኛ ቋንቋ የመጀመሪያ ዲግሪ መርሃ ግብር ምስረታ ስነ ስርአት ዛሬ በቤጂንግ እየተካሄደ መሆኑን በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።

ትምህርቱ የሚሰጠው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና የቤጂንግ የውጭ ጥናቶች ዩኒቨርሲቲ ባደረጉት የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት አማካኝነት ነው።

በስምምነቱ የቤጂንግ የውጭ ጥናቶች ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርትን በመጀመሪያ ዲግሪ ደረጃ ይሰጣል።
በዚሁ መሰረት የአማርኛ ቋንቋ በቻይና የትምህርት ተቋም ለመጀመሪያ ጊዜ ይሰጣል።

የምስረታ መርሃ ግብሩ ላይ የቤጂንግ የውጭ ጥናቶች ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ጂያ ውንጂንና በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተወካይ አቶ ሳሙኤል ፍጹምብርሃን መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Click to comment

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top