Connect with us

የብር ለውጡን በተመለከተ ፓርቲዎች የሰጡት አስተያየት

የብር ለውጡን በተመለከተ ፓርቲዎች የሰጡት አስተያየት
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

የብር ለውጡን በተመለከተ ፓርቲዎች የሰጡት አስተያየት

ምናባዊ ወግ | የብር ለውጡን በተመለከተ ፓርቲዎች የሰጡት አስተያየት
~ ህወሓት

ይህ የአሀዳውያን ሴራ ነው።ገንዘቡን ብቻ ሳይሆን ገና አገሩን ይሸጡታል፣

~ ኦነግ
በተለይ አስር ብሩ ላይ ያለው ሰውዬ የነፍጠኛ ተምሳሌት ነው። ለውጡ በነፍጠኛ ተጠልፏል የምንለውን አንድ ማሳያ ነው፣

~ አብን
በብሩ ላይ የነበሩ ምልክቶች መቀያየር የአማራ የጥላቻ ትርክት ውጤት ነው ብለን እናምናለን፣

~ ባልደራስ
መጀመሪያ መሪያችን እስክንድር የታገለበት መሬት ወረሩ፣ ኮንደምኒየም ዘረፉ አሁን ደግሞ ብርን በመቀየር ስም የኦሮሞን የበላይነት የማንገስ ህልም ጀምረውታል።ፍርዱን ለአዲስአበባ ህዝብ እንተዋለን።

~ ኢዴፓ
የፓርቲያችን አባል አቶ ልደቱን ሲያስሩት ህገወጥነቱ እንደሚፋፋም ተናግረን ነበር፣

~ ኢዜማ
የብር ለውጡ ኢንፍሌሽን እንደሚያስከትል የማያጠራጥር ነው። ግን ለውጡ ገና ለጋ በመሆኑ መታገስ ያስፈልጋል፣

~ ኦፌኮ
ጉልቻ ቢቀያየር ወጥ አያጣፍጥም። አሁን መንግስት የሚያዋጣው በግፍ ያሰራቸውን አባሎቻችንን ቢፈታ ነው።
#ጫሊ_በላይነህ

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top