Connect with us

ህወሓት 100% አሸነፈች!

ህወሓት 100% አሸነፈች!
Photo: Social Media

ፓለቲካ

ህወሓት 100% አሸነፈች!

ህወሓት 100% አሸነፈች!
=====
(አብርሀ ደስታ)

በትግራይ ምርጫ ኮሚሽን መሰረት

ህወሓት፥ 2,590,620 ድምፅ
ባይቶና፥ 20,839 ድምፅ
ውናት፦ 18,479 ድምፅ
ሳወት፦ 3,136 ድምፅ
ዓዴፓ፦ 774 ድምፅ አግኝተዋል።

በምርጫ ሕጉ መሰረት 152 (80%) የምክርቤት ወንበር በአብላጫ ውጤት የሚያዝ ሲሆን የተቀሩት 38 (20%) ወንበሮች ደግሞ በተመጣጣኝ ቅይጥ (ለ100,000 ድምፅ አንድ ወንበር) ይሰጣል።

በአብላጫ ድምፅ (First Past the Post) በሚወሰነው 152 የምክርቤት ወንበር ህወሓት 100% አሸንፏል። ለተቀረው 20%ም ህወሓት ሙሉ በሙሉ ትወስደዋለች። ምክንያቱም በድምር ከ100,000 በላይ ድምፅ ያገኘ ሌላ ተፎካካሪ ፓርቲ የለም።

ስለዚህ ህወሓት 100% አሸንፋለች።

በተለየ ሁኔታ ለተመደበው 20% የምክርቤቱ ወንበር ለተፎካካሪ ፓርቲዎቾ ለመስጠት ህወሓት ፈቅዳለች እየተባለ ነው። ሕጋዊ ባይሆንም ህወሓት 38ቱ ወንበሮች ለተፎካካሪዎች ብታበረክት መልካም ነው እላለሁ። ወጣቶቹ ፖለቲከኞች በምክርቤት ተወክለው የህዝብ ስሜትና ፍላጎት ቢያንፀባርቁ ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም!

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top