Connect with us

ቤት ያልደረሳቸው ነዋሪዎች በማህበር ተደራጅተው የጋራ ቤት እንዲገነቡ ተወሰነ

ቤት ያልደረሳቸው ነዋሪዎች በማህበር ተደራጅተው የጋራ ቤት እንዲገነቡ ተወሰነ

ማህበራዊ

ቤት ያልደረሳቸው ነዋሪዎች በማህበር ተደራጅተው የጋራ ቤት እንዲገነቡ ተወሰነ

ለ20/80 እና 40/60 ተመዝጋቢ ሆነው ቤት ያልደረሳቸው ነዋሪዎች በማህበር ተደራጅተው የጋራ ቤት እንዲገነቡ ተወሰነ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የመኖሪያ ቤት ችግርን ለመቅረፍ ለ20/80 እና 40/60 ተመዝጋቢ ሆነው ቤት ላልደረሳቸው ነዋሪዎች አማራጭ የመፍትሄ ሀሳብ አስተላልፏል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በዛሬው ዕለት 30ኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሂዷል።

ጉባኤው በተለያዩ አጀንዳዎች ዙሪያ የተወያየ ሲሆን÷ በከተማዋ የሚታየውን የመኖሪያ ቤትና የትራንስፖርት ችግር ከመፍታት አንፃር አፅንኦት ሠጥቶ ተወያይቷል።

ችግሮቹን ለመፍታትም ካቢኔው በተለያዩ አማራጮች ሃሳቦች ዙሪያ ሠፊ ውይይት አድርጎ ውሳኔውን አስተላልፏል።

በዚሁ መሰረት የመኖሪያ ቤት ችግርን ለመቅረፍ ለ20/80 እና 40/60 ተመዝጋቢ ሆነው ቤት ያልደረሳቸው ነዋሪዎች በማህበር ተደራጅተው የጋራ ቤት ለመገንባት እንዲችሉ ከተማ አስተዳደሩ የመሬት እና የግንባታ ግብዓት በማቅረብ እራሳቸው እንዲገነቡ ለማድረግ አማራጭ የመፍትሄ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

ከዚያም ባለፈ በከተማዋ የሚስተዋለውን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ 400 አውቶቢሶች ግዢ በልዩ ሁኔታ እንዲከናወን እና በብልሽት አገልግሎት መስጠት ያቆሙ 125 አውቶቡሶች በአስቸኳይ አስፋላጊው ጥገና ተደርጎላቸው ከአዲስ አመት የመጀመሪያ ቀናት ጀምሮ አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ውሳኔ ተላልፏል ፡፡

የማህበር ቤት ልማት መመሪያ እና ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ቢሮ በቀጣይ ዝርዝር መረጃ የሚሰጥ መሆኑን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬተሪያት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

#FBC

Click to comment

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top