Connect with us

ሶስት ሚልየን ቶን ሲሚንቶ ከውጭ ለማስገባት ተወሰነ

ሶስት ሚልየን ቶን ሲሚንቶ ከውጭ ለማስገባት ተወሰነ
Photo: Social Media

ኢኮኖሚ

ሶስት ሚልየን ቶን ሲሚንቶ ከውጭ ለማስገባት ተወሰነ

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል እንደገለፁት የተፈጠረውን የሲሚንቶ ችግር ለመቅረፍ የፋብሪካዎችን የማምረት አቅም ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ለሲሚንቶ እጥረት መከሰት በዋናነት የመለዋወጫ ችግር፣ የኤሌክትሪክ መቆራረጥ፣ የግብዓት እጥረት ፣ የአመራርና የባለሙያ የክህሎት ክፍተት መኖር፣ የፀጥታ ችግር፣ የጥሬ እቃ አቅርቦት እና ሌሎች ችግሮች መኖራቸው ነው ያሉት አቶ መላኩ ችግሩን ለመቅረፍ ከባለድርሻ አካላት ጋር በትኩረት በመሰራቱ መሻሻል መታየቱን ተናግረዋል፡፡

በፋብሪካዎች ላይ እየተፈጠረ ያለውን የመለዋወጫ ችግር ለመቀረፍ 85 ሚሊዮን ዶላር ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የገለፁት ሚኒስትሩ ይህም የፋብሪካዎችን የማምረት አቅም ወደ 63 በመቶ ከፍ እንዳደረገው ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም ወቅታዊውን ችግር ለመቅረፍ 3 ሚሊዮን ቶን ሲሚንቶ ከውጪ ለማስገባት መወሰኑን ገልፀዋል፡፡

በመጨረሻም በዘላቂነት የሲሚንቶን የገበያ ችግር ለመፍታት መመሪያ መዘጋጀቱንና ከሚቀጥለው ሰኞ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡(ንኢሚ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top