Connect with us

ጉቦኞች ተያዙ

ጉቦኞች ተያዙ
Photo: Social Media

ወንጀል ነክ

ጉቦኞች ተያዙ

በጉለሌ ክፍለከተማ ወረዳ 10 ከመሬት ጋር በተያያዘ አገልግሎት ለማግኘት ወደ መስሪያ ቤቱ የሄዱ ተገልጋዮችን ጉዳይ እናስፈጽማለን በሚል ጉቦ ሲቀበሉ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በወንጀል ድርጊቱ ውስጥ በመንግስት መዋቅር ውስጥ ከክፍለከተማ እስከ ወረዳ ከተዘረጋው ሰንሰለት በተጨማሪ ደላሎችም ይገኙበታል፡፡

ለከንቲባ ጽ/ቤት በመጣ ጥቆማ የፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ከተገልጋዮቹ ጋር በመሆን ባደረገው ተከታታይ ክትትል በዛሬው ዕለት ለአገልግሎት እንዲከፈላቸው የጠየቁትን ገንዘብ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ህብረተሰቡም በህጋዊ መንገድ ማግኘት የሚችለውን አገልግሎት ገንዘብ በመቀበል በህገ-ወጥ መንገድ አገልግሎት የሚሰጡ የመንግስት አካላትን በማጋለጥ ግዴታውን እንዲወጣ የከተማ አስተዳደሩ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

የወንጀል ድርጊቱን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃዎች በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ በኩል ለህዝብ ይፋ የሚደረጉ ይሆናል።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top