Connect with us

የምግብ ዘይት፣ ስኳር፣ የዳቦ ስንዴ፣ ሩዝና የታሸጉ የሕፃናት ምግቦች ሙሉ ለሙሉ ከታክስ ነፃ ሆኑ

የምግብ ዘይት፣ ስኳር፣ የዳቦ ስንዴ፣ ሩዝና የታሸጉ የሕፃናት ምግቦች ሙሉ ለሙሉ ከታክስ ነፃ ሆኑ
Photo: Social Media

ኢኮኖሚ

የምግብ ዘይት፣ ስኳር፣ የዳቦ ስንዴ፣ ሩዝና የታሸጉ የሕፃናት ምግቦች ሙሉ ለሙሉ ከታክስ ነፃ ሆኑ

መንግሥት የሸቀጦችን ዋጋ በማረጋጋት ኅብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ በአምስት መሠረታዊ የምግብ ሸቀጦች ላይ ተጥሎ የነበረውን ቀረጥ ሙሉ ለሙሉ ማንሳቱ ተገለጸ።

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ወንድሙ ፍላቴ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ መንግሥት በምግብ ሸቀጦች ላይ እየታየ ያለውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት የምግብ ዘይት፣ ስኳር፣ የዳቦ ስንዴ፣ ሩዝና የታሸጉ የሕፃናት ምግቦችን ሙሉ ለሙሉ ከቀረጥና ታክስ ነፃ አድርጓል፡

መንግሥት ከእነዚህ ምርቶች ያገኝ የነበረውን ገቢ ሙሉ ለሙሉ በመሰረዝ ምግቦቹን ከውጭ ለሚያስገቡ ነጋዴዎች ቀረጥና ታክሱን ነፃ አድርጎ ኅብረተሰቡ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ማግኘት ያለበትን መሠረታዊ የምግብ ሸቀጥ በቀላሉ እንዲያገኝ እገዛ እያደረገ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ፤ ከዚሁ ጎን ለጎንም አቅርቦቱ እንዲሻሻልና ጥራቱ እንዲጨምር እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።

የምግብ ዘይትን በተመለከተ ከዚህ በፊት በመንግሥት ድጎማ ይገባ የነበረው ፓልም ወይም በተለምዶ የሚረጋው ዘይት መሆኑን ያስታወሱት ዳይሬክተሩ፤ በአሁኑ ወቅት ሙሉ ለሙሉ ይዘታቸው ፈሳሽ የሆኑ እና በቫይታሚን ኤ እና ዲ የበለፀጉ የዘይት ምርቶች ከዚህ በፊት በተመረጡ 24 አስመጪዎች እንዲገቡ እየተደረገ መሆኑን አብራርተዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘም ማንኛውም አስመጪና የግል ነጋዴ እነዚህን ምርቶች ከውጭ ሲያስገባ ከቀረጥ ነፃ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ስርጭቱንና ዋጋውን በተመለከተ መንግሥት የሚቆጣጠራቸው መሆኑን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

እንደ አቶ ወንድሙ ገለጻ፤ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በአብዛኛው የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ በመሆኑና የአቅርቦት እጥረት እንዳይፈጠር በሚል በመንግሥት ድጎማ ብቻ ይገቡ የነበሩ ምርቶች በግል ነጋዴዎች ጭምር እንዲገቡ ተደርጓል።ይህ የሆነው አቅርቦቱ እንዳይቋረጥና ነጋዴውም ተገቢውን ትርፍ እንዲያገኝ ለማስቻል ነው።

ነገር ግን ከዚህ ባለፈ ነጋዴው ባልተገባ መንገድ እንዳይጠቀምና ምርቱ ወደ ግለሰቦች እጅ እንዳይገባ መንግሥትጥብቅክትትልያደርጋል።

በአገሪቱ ከሚያስፈልገው የምግብ ዘይት ስድስት በመቶ በአገር ውስጥ የሚመረት መሆኑን ጠቅሰው፣ ቀሪው ከውጭ የሚገባ መሆኑን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል። በአጠቃላይ በአገር ውስጥ የሚመረተውን የምግብ ዘይት ጨምሮ በግለሰብ ነጋዴዎችና በአስመጪዎች በየወሩ እስከ 42 ሚሊዮን ሌትር የምግብ ዘይት እየገባ መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።

(ምንጭ:- አዲስ ዘመን ነሀሴ 12 ቀን 2012)

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top