Connect with us

ሺህ ውሸት ቢከመር አንድ እውነት አይወጣውም!

ሺህ ውሸት ቢከመር አንድ እውነት አይወጣውም!
Main photo: The Blue Nile Falls near Bahir Dar in 2006. Photo by CT Snow

ባህልና ታሪክ

ሺህ ውሸት ቢከመር አንድ እውነት አይወጣውም!

ሺህ ውሸት ቢከመር አንድ እውነት አይወጣውም!
(ሲሳይ አለማየሁ)

የግብፅ የማደናገሪያ እንቅፋቶች አገር ከማተራመስ፣ የፖለቲካና የኢኮኖሚ አሻጥር ከማድረግ፣ የዲፕሎማቲክ ሴራ ከማሴር፣ ታሪክ ከማዛባት፣ ከወታደራዊ ቀረርቶ አልፎ አሁን ሳይንስን የማዛባት ካርታ እስከ መምዘዝ ደርሷል።

እስከ አሁን ባደረጉት ሙከራ የተሳካላቸው ነገር ቢኖር የገንዘብ እርዳታ ወይንም ብድር እንዳናገኝ ያደረጉት ጥረት ነው። እርሱም ኢትዬጵያ በልጆቿ፣ ቆራጥነት ከሽፎ ታላቁ ግድብ አሁን የደረሰበት ደረጃ ደርሷል። አሁንም እንኳን ደስ አለን። እኛው እንደ ጀመርን እኛው እንጨርሰዋለን።

ከአሁን በፊት ግድብ ለደህንነታችን ያሰጋል የሚል ጥያቄ አቅርበው ነበር። ስጋቱ ተገቢ ነው። 74 ቢሊዬን ሜትር ኩብ ውሃ እላያቸው ላይ ተንጣሎ ለምን ሰጋችሁ አይባልም። ግድቡ ከፈረሰ የሚያስከትለው እልቂት ቀላል አይደለም። ኢትዮጵያም ይህን ስላመነች በአለም እውቅ የሆኑ ባለሙያዎች የግድቡን አስተማማኝነት አስጠንታለች። ለዚህም 2 ከጀርመን 1 ከግብፅ 1 ከሱዳን 1 ከአዲስ አበባ በተውጣጡ የግድብ ምህንድስናና የጅኦ ፊዚክስ ባለሙያዎች እንዲያጠኑት ተደርጎ ሁሉም ግድብ አስተማማኝና አለም አቀፍ መስፈርትን ያሟላ መሆኑን በመመስከር ለግብፅም ሆነ ለሱዳን ስጋት እንደማይሆን አረጋግጠዋል።

እና አሁን እየተመዘዘ ያለው ካርታ ምንድን ነው? ከ140 ሚሊዮን በላይ ለሚኖርባቸው ግብጽን ሱዳን አሁንም ይህ ግድብ ከፈረሰ አደጋ ነው ይሉናል። በጥናት ከተረጋገጠ በኋላ አሁን የተመዘዘው ጨዋታ የመሬት መንቀጥቀጥ ነው። ለዚህ ሳይንስን በማዛባት አንድ አባስ ሽርክ የተባለ የጅኦሎጅ ፕሬፌሰር ጥናት ይዘው ብቅ ብለዋል። እንደ ፕሮፌሰሩ የኢትዮጵያ ስምጥ ሸለቆ (Rift Valley) ለመሬት መንቀጥቀጥ የተጋለጠ ስለሆነ ይህ መንቀጥቀጥ ግድቡን ሊያፈርሰው ይችላል ይላሉ። ኢትዮጵያ በአለፉት አመታት ከማግኒትድ 4 እስከ ማግንቲዮድ 5 የሚደርስ ውድ አምስት ጊዜ የመሬት መቀጥቀጥ ደሶባታል ይላሉ።

ይህ ጥናትና ስጋት በእውነቱ ከአንድ ፕሮፌሰር አይጠበቅም። ምክንያቱም በሪፍትቫሊ እና በግድቡ መካከል ያለው ርቀት ከአፋር እስከ ግድቡ 500 ኪሎሜትር ነው። ከላይ የተጠቀሰው የመሬት መንቀጥቀጥ መጠን አምስት መቶ ኪሎሜትር ላይ በጥንቃቄ የተሰራን አለም አቀፍ ደረጃን የጠበቀ ግድብ ከቶውንም ሊያሰጋ አይችልም። ይህን አድሎ የተሞላበት የግብፁን ፕሮፌሰር ዘገባ እውቁ የኮሎራዶ ፕሮፌሰር ሮጀር ቢልሃም ፉርሽ ያደርጉታል። እንደ ፕሮፌሰር ቢልሃም እንዲህ አይነት የመሬት መንቀጥቀጥ ከ 200ኪ.ሜ በላይ ጉዳት ማድረስ እንደማይችል ይናገራሉ።

አሁንም ሲሻቸው በጥናት የተረጋገጠውን የግይብ ብቃት የ74 ቢሊዮን ውሃ ግፊት ግድቡን እንዲንሸራተት ያደርገዋል እያሉ ወደኋላ ሊመልሱን ይዳዳቸዋል።

ግብፅ ሆይ የተንኮል ካርታችሁ ተመዞ አልቋል። ለጋራ ጥቅም በጋራ እንስራ እላለሁ።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top