Connect with us

ኦሮሞን በኢኮኖሚ ማሽመድመድ-የኦሮሞ ተቆርቋሪ ነን ባይ ፖለቲከኞች …

ኦሮሞን በኢኮኖሚ ማሽመድመድ-የኦሮሞ ተቆርቋሪ ነን ባይ ፖለቲከኞች የትግል ስልት፤
Photo: Social Media

ህግና ስርዓት

ኦሮሞን በኢኮኖሚ ማሽመድመድ-የኦሮሞ ተቆርቋሪ ነን ባይ ፖለቲከኞች …

ኦሮሞን በኢኮኖሚ ማሽመድመድ-የኦሮሞ ተቆርቋሪ ነን ባይ ፖለቲከኞች የትግል ስልት፤
ከስናፍቅሽ አዲስ

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ በኦሮሞ ህዝብ ላይ የደረሰው በደል ቁጥርም ስፍርም የለውም፡፡ ይሄ ተደጋጋሚ በደል በራሱ ልጆችም በሌሎችም ቅንጅት የሚፈጸም መሆኑ ደግሞ ይበልጥ ጉዳቱን ያከፋዋል፡፡ ባለፉት ሃያ ሰባት አመታት የኦሮሞ ህዝብ የበደል ጽዋ ሲሞላ መከራውን ወደ ጽዋው ይከቱ የነበሩት የራሱ ልጆች ነበሩ፡፡ ያንን ሁሉ አልፎ አዲስ ቀን መጣልኝ ሲል የእኛ ቀን ካልመጣ ያንተ ቀን ቀናችን አይደለም ያሉ ፖለቲከኞች ዳግም ለመከራ ዳረጉት፡፡

ብዙዎቹ የኦሮሞ የፖለቲካ ልሂቃን ችግሩን ከመጋፈጥ ሩቅ ሀገር መሸሽን ይመርጣሉ፡፡ ልጆቻቸውን ዜግነት አስቀይረው ሚስቶቻቸውን አስተማማኝ ሀገር አስጠግተው ከሥራ ሰዓት በተረፋቸው ጊዜ ህዝቡ ያስቀየመውን መንግስት ለመጣል ስራውን እንዳይሰራ ይቀሰቅሱታል፡፡

የኢትዮጵያ ታላላቅ ከተሞች መሆን የሚገባቸው የግብርና ኢኮኖሚ ማዕከል የሆኑ ከተሞች እንዳያድጉ እንዲህ ያለው የራስን ልጅ የሚበላ ፖለቲካ ማነቆ ሆኗል፡፡ በሃያ አምስት አመት ፖለቲካ ውስጥ እንኳን መቀሌ፣ ሀዋሳና ባህር ዳር እንዲህ ባለው ጥራት ሲከተሙ የጥንቶቹ ነቀምትና አምቦ ካሉበት ፈቅ አሉ የሚል ዜና አልሰማንም፡፡

ከኦሮሚያ ከተሞች የተሻለ የንግድ እንቅስቃሴ፣ የአብሮነት እሴትና የጋራ መስተጋብር አላት በሚል የምትወደሰው ሻሸመኔ ይሄንን ስም እንድታጣ፣ የንግድ እንቅስቃሴዋ እንዲከስም፣ ስሟ እንዲጠለሽ፣ ለሰው ልጅ ህይወት አደጋ ናት እንድትባል ያለማቋረጥ እየሰሩ ያሉት እነኚሁ ለኦሮሞ ፖለቲካ እንቆረቆራለን የሚሉ ልሂቃን ናቸው፡፡

ተደጋጋሚ አመጽ፣ ልጅ የአባትን የጫት እርሻ እንዲያወድም ጥሪ፣ የሰላሌ ኦሮሞን ሀረር ሀገርህ አይደለም፤ ለባሌ መጤ ነህ የሚል የህዝቡን አንድነት የሚሸረሽር የፖለቲካ ዘይቤ በመከተል ከፍ ያለውን መልሶ ዝቅ የማድረግ ጠባይ ሲደጋገም ኖሯል፡፡

የሰሞኑ አመጽ ጥሪም ሐረርጌን ዳግም በኢኮኖሚ የማዳከም ዘመቻ ይመስላል፡፡ የንግድ እንቅስቃሴውን ማገት፣ የህዝቡን የዕለት ተዕለት ሕይወት ማደናቀፍ፡፡ ህዝቡ ጉዳዩን የነቃበት ይመስላል፡፡ ጥሪ ከአፋቸው ሳይወጣ ከስሟል፡፡ ዘላቂ ነው አይደለም አብረን እናየዋለን፡፡ እስከ መቼ ህዝቡ ይሰቃያል የሚለው ግን ምላሽ ይሻል፡፡

የማዶዎቹ ፖለቲከኞች የኢንቨስትመንት ገበያቸውን ሲቀሰቅሱ ንብረት የማይወድምበት፣ ጨዋ ህዝብ ያለበት፣ አስተማማኝ ሰላም የተረጋገጠበት እያሉ ኦሮሚያን በአመጽ ለማናወጥ፣ ኢንቨስትመንት ሲወድም የትግል ስልት ነው ብሎ የማወደስ፣ ሰላም ሲጠፋ አራት ኪሎ ይናወጣል በሚል ምኞት ብቻ በርቱ የማለት ቅስቀሳው መንቃት አለብኝ የሚል የኦሮሞ ወጣት ካልፈጠረ ኪሳራው ጊዜ የማይወስድ ይሆናል፡፡

ደርግንም ቢሆን የታገሉት የኦሮሞ ልጆች በክብር ቤተ መንግስቱን ሲቆጣጠሩ ያኔ ትግል በርቀት ነው ያሉ እንደ እንግዳ በቦሌ ሲገቡ አይተናል፡፡ ትናንት ወያኔ ስር ሆነው ወያኔን ታግለው ድል ያደረጉት ድላቸውን ሲያበስሩም ኑ ሲባሉ በቦሌ የገቡት ዛሬም ሩቅ ሆነው ወጣቱን ስለማታገል የሚያስቡ እንጂ ከሚዘጋው መንገድ የሚዘጋ ጉሮሮ ያላቸው፣ ከሚራበው ወገን ጋር ረሃብን የማይጋሩ፣ ከሚወድቀው የህዝቡ ኢኮኖሚ ጋር ኢኮኖሚያቸው የማይወድቅ ናቸው፡፡

ምናልባትም የዲያስፖራ ፖለቲካን ስናስደርሰው ድርሻውን እንድናስብ ከሚጋብዙን የታሪክ አጋጣሚዎች በጥቂት የኦሮሞ ልሂቃን የባህር ማዶ ቅስቀሳ የምንመለከተው ድርብ አንጀትነት ይመስለኛል፡፡

( ማስታወሻ ከአዘጋጁ:- ይኸ መጣጥፍ የፀሐፊውን እንጂ የድሬቲዩብን ኤዲቶሪያል አቋም አያሳይም።)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top