Connect with us

ፖሊስ በአቶ በቀለ ገርባ ላይ ሲያካሂድ የነበረውን የምርመራ ሥራ ማጠናቀቁን ገለፀ

ፖሊስ በአቶ በቀለ ገርባ ላይ ሲያካሂድ የነበረውን የምርመራ ሥራ ማጠናቀቁን ገለፀ
Photo: Ethiopian Reporter

ህግና ስርዓት

ፖሊስ በአቶ በቀለ ገርባ ላይ ሲያካሂድ የነበረውን የምርመራ ሥራ ማጠናቀቁን ገለፀ

የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ የምርመራ ቡድን በአቶ በቀለ ገርባ ላይ ሲያካሂድ የነበረውን የምርመራ ሥራ ማጠናቀቁን አስታወቀ።ምርመራው መጠናቀቁን ተከትሎ እስካሁን ሲታይ የነበረው የጊዜ ቀጠሮ የምርመራ ሰነድ ተዘግቶ አዲስ ወደተከፈተው ቀዳሚ ምርመራ እንዲዛወርለት በትላንትናው ዕለት ጠይቋል። የቀዳሚ ምርመራ ችሎት የሚባለው ዐቃቤ ሕግ የምርመራ መዝገቡን ከፖሊስ ተቀብሎ ተጠርጣሪው ላይ የተደረገው ምርመራ ተአማኒ መሆኑን ሲያረጋግጥ የማስረጃ ጥበቃ ለማድረግ የሚከተለው ሥርዓት ነው።

በዚህ መሠረት ሕጉን ተከትሎ የቀዳሚ ምርመራ ፋይል በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ አራዳ ምድብ ያስከፈተ በመሆኑ፣ ይህ የጊዜ ቀጠሮ ሲመለከት የነበረው ችሎት መዝገቡን ዘግቶ ወደ ቀዳሚ ምርመራ ችሎት እንዲመራው የምርመራ ቡድኑ እና ዐቃቤ ሕግ ጠይቋል። የምርመራ ቡድኑ በአቶ በቀለ ገርባ በተሰጠው ጊዜ የተለያዩ የምርመራ ሥራዎች ማከናወኑን ለአራዳ ምድብ ችሎት አስታውቋል።

በዚህም በአዲስ አበባ ከተማ እና አካባቢዋ እንዲሁም በሻሸመኔ ሰኔ 23 እና 24 ቀን 2012 ዓ.ም በነበረው ብጥብጥ የደረሰውን ውድመት አስመልክቶ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ዘርፉን የተመለከተ 45 ገጽ ያካተተ ማስረጃ ማቅረቡን ጠቅሷል።ተጠርጣሪው የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ አስከሬን በአስገዳጅ መልኩ ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ 10 ቀናት በማስለቀስ የምኒልክ ሐውልት ማፍረስ እና ቤተ መንግሥቱን መቆጣጠር ይቻላል የሚል ትእዛዝ መስጠቱን በማስረጃ ማረጋገጡን ፖሊስ ገልጿል።
ከተጠርጣሪው የተገኙት ሁለት ሽጉጦች ሕገ ወጥ መሆናቸውንም ፖሊስ ጠቅሷል።የተጠርጣሪው ጠበቆች ደንበኛቸው ፈጸሙ የተባለው ወንጀል አመላካች ነገር አልሰማንም፤ በመሆኑም ፍርድ ቤቱ የምርመራ መዝገቡን አቅርቦ እንዲመረምር እና ይህ የምርመራ መዝገብ ተዘግቶ ጉዳዩ በቀዳሚ ምርመራ ይታይ ቢባል እንኳን ተጠርጣሪው የዋስ መብታቸው እንዲከበር አመልክተዋል። አቶ በቀለ ገርባ በበኩላቸው የፈጸምኩት ወንጀል የለም፤ እኔ የፖለቲካ መሪ እንጂ የምመራው ሠራዊት የለም፤ በመሆኑም በብሔር እና በሃይማኖት ግጭት የተከፈተብኝ ወንጀል እኔን የሚመለከት አይደለም ብለዋል።

ዐቃቤ ሕግ በበከሉ በተጠርጣሪው ላይ የሕዝብ ለሕዝብ ግጭት በመቀስቀስ እና በሌሎች ወንጀሎች ተጨባጭ ማስረጃ ማግኘቱን በማስታወቅ፣ ይህንን ማድረግ የሚቻለው በጊዜ ቀጠሮ ችሎት ሳይሆን በመደበኛ ክርክር ነው ብሏል።አቶ በቀለ የተጠረጠሩበትም ወንጀል የሰው ሕይወት የጠፋበት እና ከባድ በመሆኑ የዋስትና መብታቸው ሊጠበቅ አይገባም ሲል ለፍርድ ቤቱ አመልክቷል።ፍርድ ቤቱ በበኩሉ የፖሊስን የምርመራ መዝገብ መርምሮ ትእዛዝ ለመስጠት ለሐምሌ 29 ቀን 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።በሌላ በኩል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ጃዋር መሐመድን ጨምሮ በ14 ተጠርጣሪዎች ላይ የቀዳሚ ምርመራ ፋይል በሌላ ችሎት ማስከፈቱን ገልጿል። (ETV)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top