Connect with us

የመከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አደም መሐመድ ይናገራሉ:-

“ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨት የሚደረጉ ሴራዎች ካሁን በኋላ ቦታ የላቸውም”- የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም
Photo: EPA

ህግና ስርዓት

የመከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አደም መሐመድ ይናገራሉ:-

~ ከህግ ውጪ ሆኖ፤ በተለይ በሕዝቦች መካከል ቁርሾ በመፍጠር፤ ግጭት በመፍጠር፤ በሃይማኖትና በተለያዩ ምክንያቶች ሰዎች እየተፈረጁ ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨት የሚደረጉ ሴራዎች ካሁን በኋላ ቦታ አይኖራቸውም፣

~ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ፤ ሃይማኖትን ከሃይማኖት የሚያጋጩ፤ ጎሳን ከጎሳ የሚያጋጩ ስራዎች ሆነ ተብለው የሚሰሩ ከሆነ፤ አድገው ወደ ዘር ማጥፋት፣ ወደ እልቂት የሚያመሩ በመሆኑ መንግስት እርምጃ ይወስዳል፣

~ ” መንግስትና የመከላከያ ሰራዊት ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ እና አገርን የሚበትንና የሚያዳክም ማንኛውም ህገወጥ የሆኑ ተግባራትን እያዩ ዝም አይሉም ፡፡

~ የጸጥታ ተቋማት የማንም ፓርቲ ዕሴት ወይም ሀብት ሳይሆኑ የኢትዮጵያ ሀብት ናቸው። በአንድ ፓርቲ ፕሮግራም ሊቀረጽና ሊገነባ አይገባውም።

~ የሰራዊቱም ጥንካሬ ከአንድ ፓርቲ የፖለቲካ ጥንካሬ የሚነሳ መሆን የለበትም፡፡ ከአንድ ፓርቲ የፖለቲካ ጥንካሬ የሚነሳ ከሆነ፤ ፓርቲው ሲጠነክር አብሮ የሚጠነክር ይሆናል፡፡ ሌላውን እያዳከመ የሚኖርም ይሆናል፡፡ ያ ፓርቲ ሲደክም፣ ነገ በሌላ መንገድ ወደ ስልጣን የሚመጣ ኃይል ደግሞ የሚንደውና የሚያፈርሰው መሆን የለበትም።

~ ፓርቲዎች በራሳቸው በሚያደርጉት ጭቅጭቅና ንትርክ ይሄንን ተቋም መጠቀሚያ የሚያደርጉበት ሁኔታ ከተፈጠረ የሆነ ፓርቲ ወደስልጣን በመጣ ቁጥር እየወደቀና እየፈረሰ እንደገና የሚገነባ ይሆናል፡፡ እየፈረሰ እየተገነባ የሚሄድ ተቋም ደግሞ ይህችን ታላቅ አገር አይመጥንም።

~ በህገ መንግስቱ መሰረት ሰራዊቱ ከፖለቲካ ገለልተኛ መሆን አለበት፤ በፖለቲካ ጉዳዮች እጁን አያስገባም ፣የፖለቲካ አዋላጅም መሆን እንደሌለበት በግልጽ ተቀምጧል፣

~ “ኢትዮጵያን እኔ ከሌለሁ ትፈርሳለች ወይም እኔ ካልተጠቀምኩ እናፍርሳት የሚለው አካል ሁል ጊዜ ቢናገርም፤ በእኔ በኩል ኢትዮጵያን የምትፈርሰው መጀመሪያ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ላይ የሚያምኑት ሕዝቦቿ እና መሪዎቿ ከሌሉና ከሌሉ ብቻ ነው ፡፡ ከዛ በላይ ኢትዮጵያ የምትፈርሰው የመከላከያ ኃይላችን፣ የፀጥታ ኃይላችን፣ የደህንነት ኃይላችን ሲፈርስ፤ ወይም እሱ መስዋዕት ሆኖ ሲሸነፍ ብቻ ነው::

(አዲስ ዘመን፤ ሐምሌ 18/2012)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top