Connect with us

የፌደራል ፍርድ ቤቶች ሥራ የሚያስጀምር መመሪያ እየተዘጋጀ ነው

የፌደራል ፍርድ ቤቶች ሥራ የሚያስጀምር መመሪያ እየተዘጋጀ ነው
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

የፌደራል ፍርድ ቤቶች ሥራ የሚያስጀምር መመሪያ እየተዘጋጀ ነው

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ ቤቶች የኮቪድ-19ን በመከላከል መደበኛ አገልግሎት መስጠት የሚያስችላቸው መመሪያ ለማውጣት ረቂቅ መመሪያ እያዘጋጀ መሆኑን ገለጸ፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በሃገራችንም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቅርብ ጊዜ መፍትሔ እንደማይኖረው ከግምት ውስጥ በማስገባት የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ወርሽኙን በመከላከል መደበኛ አገልግሎታቸውን መስጠት የሚችሉበትን ሁኔታ ለማመቻቸት እየሰራ ይገኛል፡፡

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በሃገራችን የኮቪድ 19 ወርሽኝን ስርጭት ለመግታትና ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ፍርድ ቤቶች ከመጋቢት 10 ቀን 2012 ዓ.ም በከፊል ዝግ ሆነው አስቸኳይነት ያላቸው ጉዳዮች ብቻ በተረኛ ችሎት እንዲያስተናግዱ እስከ ሐምሌ 10 ቀን 2012 ዓ.ም መወሰኑ ይታወቃል፡፡

ነገር ግን ፍርድ ቤቶች ዜጎች በህግ አግባብ ፍትህ የሚያገኙበት ተቋማት እንደመሆናቸው ለረጅም ጊዜ በከፊል ዝግ ሆነው መቆየት እንደሌለባቸው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በጽኑ ይገነዘባል፡፡

በመሆኑም ጠቅላይ ፍ/ቤቱ በኮቪድ 19 ዘመን ወረርሽኙን በመከላከል ዜጎች ፍትህ በሚጠይቁባቸው ጉዳዮች ላይ ፍርድ ቤቶች መደበኛ አገልግሎ መስጠት የሚያስችላቸውን ወጥ አሰራር ለመዘርጋት የሚመሩበት ረቂቅ መመሪያ እየተዘጋጀ መሆኑን ጠቁሟል፡፡ የረቂቅ መመሪያው ዝግጅት ሲጠናቀቅም የህግ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ግብአት እንዲሰጡበት ከተደረገ በኋላ ስራ ላይ እንዲውል ይደረጋል ብሏል፡፡

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ከሐምሌ 10 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን “በኮሮና ቫይረስ (COVID 19) ምክንያት የተከሰተውን ሀገራዊ ሁኔታ አስመልክቶ ፍርድ ቤቶች ሊመሩበት የሚገባ አጠቃላይ መመሪያ (Comprehensive Guideline)” አውጥቷል እየተባለ የሚሰራጨው መረጃም ትክክል አለመሆኑን ገልጿል፡፡

(የ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top