Connect with us

“ምርጫችን በእጃችን ነው”

"ምርጫችን በእጃችን ነው"
Photo: Facebook

ፓለቲካ

“ምርጫችን በእጃችን ነው”

“በሌላ ጉዳይ ላይ ለመነጋገር እንችላለን፤ በመብታችን ላይ በተለይ ደግሞ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብታችን ላይ በተመለከተ ግን መደራደር አንችልም፤ በፍፁም። ይህ ቀይ መስመር ነው።

ከዚህ በታች የሆኑ ብዙ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ። “ይህን ኣምጣ ይህን ልሰጥህ” ልትል የምትችልበት። በዚህ ጉዳይ ላይ ግን ሰጥቶ መቀበል ብሎ ነገር የለም። ምርጫ መሰረታዊና ትልቅ ነገር ነው።

ዋናው ነገር የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት ነው። ያለፈው የትግል ውጤት አስጠብቆ የመሄድና ቀጣዩን የማስተካከል ጉዳይ ነው። ምክንያቱም ያለፈውን አስጠብቀን ነው ቀጣዩን ማስተካከል የምንችለው። በትግራይ እጅግ በጣም የተደራረበ ብዙ ጫና ነው ያለው።

እያልን ያለነው ግን ለምንም ጫና አንበገርም ነው። ምንም ዓይነት ጫና አይበግረንም። ግዜ ተጣበበብን ብለንም አንጨናነቅም። ሁላችንም ተጋግዘን ልንሻገረው እንችላለን።

ምርጫችን በእጃችን ነው። መብታችንም በእጃችን ነው። የመመከቱ ነገርም እንደዚሁ በእጃችን ነው። ማሟላት ያለብንን ነገር ግን ማሟላት ኣለብን። ለዚህም ጎን ለጎንም ዝግጅት ማድረግም ጀምረናል።” ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል

የህወሓት ሊቀመንበር

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top