Connect with us

ዛሬ ሀገር ከመምራት ሁሌም ተተኪውን ትውልድ መምራት ይበልጣል

ዛሬ ሀገር ከመምራት ሁሌም ተተኪውን ትውልድ መምራት ይበልጣል

ባህልና ታሪክ

ዛሬ ሀገር ከመምራት ሁሌም ተተኪውን ትውልድ መምራት ይበልጣል

ክቡር አቶ ኃይለ ማርያም ከዚህ ቀደም ሀገር መርተዋል፤ በአዲሱ ራዕይዎት ደግሞ መጪውን ትውልድ ይመራሉ፡፡ ዛሬ ሀገር ከመምራት ሁሌም ተተኪውን ትውልድ መምራት ይበልጣልና፡፡
******
ከሄኖክ ስዩም በድሬቲዩብ
መልካ ቁንጥሬ ዋልኩ፡፡ ቱሪዝም ኢትዮጵያና የቱሪዝም ጋዜጠኞች አረንጓዴ አሻራቸውን ማኖር ጀምረዋል፡፡ ገና እንቀጥላለን፡፡ እኛ የጥንቷ ኢትዮጵያ ውበት የመጪዋ ኢትዮጵያ መገለጫ እንዲሆን እንመኛለን፡፡

መልካ ቁንጥሬ ታላቅ መካነ ቅርስ ነው፡፡ በኢትዮጵያ በግሩም ሁኔታ ከተያዙ ጥብቅ የአርኪዎሎጂ ስፍራዎች አንዱ ነው፡፡ እዚያ አረፈድን፡፡ የቱሪዝም ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር አቶ ስለሺ ግርማ የጋበዟቸው የቱሪዝም ቤተሰቦች ታድመዋል፡፡

የቦርድ አባላቱም አሉ፡፡ የቦርዱ ሰብሳቢ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝም የዕለቱ እንግዳ ናቸው፡፡ እሳቸውና ባለቤታቸው አሁን ሙሉ ጊዜያቸውን አረንጓዴ ቱሪዝም ላይ አተኩረዋል፡፡ የተራቆቱ አካባቢዎች ህይወት እንዲዘሩ፣ ትውልዱ ከተፈጥሮ እንዲታረቅ መንገድ ጀምረዋል፡፡

ችግኙን ተክለን ቃላቸውን ተቀበልን፡፡ አሁን ፍላጎታቸው የሀገራቸው ተፈጥሮ ታክሞ ማየት ነው፡፡ ደስ አለኝ፡፡ ቀደም ብሎ በጨበራ ጩርጩራ ዱር ውስጥ ባትለዋል፡፡ እስከ ኦሞ ተጉዘዋል፡፡ ፋውንዴሽኑ በብሔራዊ ፓርኮች የሚሰራቸው የልማት ስራዎች ጀምሯል፡፡ አሁንም ምኞታቸውና የቀሪ ዘመን ህልማቸው እንዲህ ባለው ስራ መቀጠል መሆኑን ተናገሩ፡፡

ሰውዬው ሀገር መርተዋል፡፡ ከዚያ ቀድሞ ደግሞ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም እና ክልል መሪ ነበሩ፡፡ የሀገራቸው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመሆን ሰርተዋል፡፡ የሚበልጠውን ስራ ግን አሁን እንደጀመሩ ተሰማኝ፡፡ የእስከአሁን የወቅት ሃላፊነት ነው፡፡ የአሁኑ ግን መጪ ትውልድን የሚታደግ መሻት ነው፡፡

በልቤ በርቱ አልኩ፡፡ ከዚህ ቀደም ሀገር መርተዋል፡፡ በአዲሱ ራዕይዎት ደግሞ መጪውን ትውልድ ይመራሉ፡፡ ወደ ውበትና ህይወት ይመራሉ፤ ከተፈጥሮ ወደ መታረቅ ይመራሉ፡፡ በጸጋው ችግርን ድል ወደሚያደርግ ትውልድ ይመራሉ፡፡ ሀገር ከመምራት የሚመጣን ትውልድ መምራት መቻል ትልቅ ስልጣን ነው፡፡ የህይወት ዘመን ስልጣን፤ በራስ ላይ የሚጣል ከባድ የህሊና ሃላፊነት፡፡ ስኬትዎን ያቅርብልዎ፤

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top