Connect with us

ይቅናችሁ!!

ይቅናችሁ!!
Photo: Ethiopian Reporter

ባህልና ታሪክ

ይቅናችሁ!!

#ይቅናችሁ!!

በዋንኛነት በብልፅግና ፓርቲ እና በህወሓት መካከል ተፈጥሮ የነበረው ቀላል የሚመስል አለመግባባት እያደር ወደመካረር አሻቅቧል። መነሻው ምንም ይሁን አንዳንድ የህወሓት ሰዎች ለውጡን ለመቀበል ያለመፈለግ ስሜቶች ውስጥ ነበሩ።

እነዚህ ስሜቶች እያደጉ መጥተው ወደቃላት ጦርነት ተሻግረዋል። በዚህ ሒደት እገሌ ትክክል ነው፣ እነእገሌ ደግሞ ተሳስተዋል የሚል ሾላ በድፍን ወቀሳ ውስጥ መግባት አልፈልግም። ግን ሁለቱም ወገኖች በውስጣቸው የተፈጠረ ጥቃቅን ልዩነቶችን እንኳን ቢያንስ ተነጋግሮ፣ ተወያይቶ ከመፍታት ይልቅ በየእለቱ ሚድያ ላይ እየወጡ ዛቻ እና ስድብ ወደማሰማት አዘቅት መውረዳቸው ብዙዎችን ሲያሳዝን ከርሟል።

እናም በዛሬው እለት ወደመቀለ ያመራል የተባለው የሽማግሌዎች ቡድን በሁለቱ ወገኖች መካከል የተጠራቀሙ ጥቃቅን ልዩነቶችን በመፍታት ረገድ ቁልፍ ሚና እንደሚኖረው እምነቴ የፀና ነው።

የሽምግልና ቡድኑ በራሳቸው ተነሳሽነት የተሰባሰቡ 52 ያህል የሀይማኖት አባቶች፣ ምሁራን እና ታዋቂ ሰዎችን ያካተተ ስለመሆኑም ተሰምቷል።

አዎ!..አለመግባባት ወይንም ቅሬታዎች ለምን ተፈጠሩ አይባልም። ጥርስና ጥርስም ይጋጫል።ዋናው ነገር ያሉትን ችግሮች በቀና መንፈስ ጠረጴዛ ላይ አስቀምጦ ለመወያየት ሁለቱም ወገኖች ዝግጁ መሆናቸው ነው።

በሌላ በኩል ከየፓርቲዎቹ ጋር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ጥገኛ የሆኑ ሀይሎች አሁንም አደናቃፊነታቸውን ቀጥለዋል።
አርቁ ከጨዋታ ውጪ እንደሚያደርጋቸው ስጋት የገባቸው ሀይሎች ከወዲሁ ከጀመሩት ቂምና ጥላቻን የማስፋፉት ትርክት እንዲወጡ ሰላም ወዳድ ሀይሎች በሙሉ የበኩላቸውን ጥረት ሊያደርጉ ይገባል።

ምንም እንኳን ቀላል የማይባሉ ጥፋቶች መኖራቸው የማይካድ ቢሆንም ባለፉት 28 አመታት የህወሓት/ኢህአዴግ አስተዋፅኦ በቀላሉ የሚታይ አይደለም። እውነት ለመናገር የአሁኑ አዲስ አመራር ጠፍጥፎ የሰራው መሆኑንም መካድ እይቻልም።እናም ግጭት፣ አለመግባባት ቢኖርም በቤተሰብ ወግ ተሸማግሎ ወደእርቀ ሰላም መሻገሩ እንደአገር የሚኖረው ጠቀሜታ እጅግ የላቀ ይሆናል።

እናም ሽማግሌዎቻቸን አላማችሁ ይሳካ!!በርቱ!..ይቅናችሁ ብለናል! (ጫሊ በላይነህ በድሬቲዩብ)

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top