Connect with us

ደኑን ከጨፈጨፍነው አረንጓዴ ዘመቻው ምን ያደርጋል?

ደኑን ከጨፈጨፍነው አረንጓዴ ዘመቻው ምን ያደርጋል?

ህግና ስርዓት

ደኑን ከጨፈጨፍነው አረንጓዴ ዘመቻው ምን ያደርጋል?

ደኑን ከጨፈጨፍነው አረንጓዴ ዘመቻው ምን ያደርጋል? እንደ እንጦጦ መልማት ያለበት የየካ ተራራና ደን ዘላቂ ላልሆነ ልማት ለምን ይወድማል?
40 ሺህ ካሬ የደን ሽፋን እንዲመነጠር የወሰነው ማን ነው?
******
አዲስ አበባ ለምን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የተፈጥሮ ልማት አትማርም፡፡ ሰውዬው እንጦጦ ላይ ተአምር ሰርተው እያሳዩ ነው፡፡ ከእሳቸው የተገኘው ምርጥ ተሞክሮ እንዴት የየካን ደን በመመንጠር ይቀመራል?

አዲስ አበባ ውስጥ የከተማዋን ካቢኔና በየደረጃው ያለውን መዋቅር ተሸክሞ ያለው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀሳብ ነው፡፡ ወንዙም ተራራው አንድነት ፓርኩም የሳቸው ነው፡፡ እሳቸው እንዳሰቡት አስቦ የአዲስ አበባ መዋቅር ምን ሰራ?

ይሄንን መልስ ፍለጋ የሚደክም እንደ የካ ደን ካለው ጭፈጨፋ ጋር ይገጣጠምና እንደውም የዶክተር አብይን መንፈስ በሚቃረን መንገድ የሚጓዝ አመራር እንዳለ ይገነዘባል፡፡ አረንጓዴ አሻራ ፖለቲካ አይደለም፡፡ ለትውልድ የማሰብና ትውልድ በምቹ ምድር እንዲኖር የማድረግ ዘላቂ የልማት ስልት ነው፡፡ አዲስ አበባን ምቹ ከተማ ማድረግ የሚቻለው የከበቧትን ተራሮች እንደ እንጦጦ ዘላቂ በሚባል የአካባቢ ጥበቃ መንፈስ በማልማት ነው፡፡ በዚህ ዶክተር አብይ ሊመስገኑ ነው፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምኞት እውን የሚሆነው ግን እንጦጦ ብቻ ተአምር ሲሰራበት አይደለም፡፡ እንዲህ ያለው ልማት ለወጨጫ ለየካ ለፉሪ ያስፈልጋል፡፡ ችግኝ እየተከልን ዛፍ የሚገነድስ ልማት ሙጥኝ ካልን ትርፉ ዘጥ ዘጥ ነው፡፡

የየካ ተራራ የአዲስ አበባ ውበት ብቻ አይደለም፤ እስትንፋስና ጤና ነው፡፡ ግማሽ ክፍለ ዘመን የኖረውና ላምበረት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ዙሪያ የሚገኘው 40 ሺህ ካሬ የደን ሽፋን እንዲመነጠር የወሰነው ማን ነው?

እድሜ ጠገብ ዛፎች የሚገኙበት በሀገር በቀል ዛፎች የታጀበው የየካ ተራራ ሌላው ቀርቶ ልጆቻችን አጋም ምን እንደሆነ እንኳን ሊገነዘቡ የሚችሉበት የተፈጥሮ ቤተ ሙከራ ነው፡፡ የሚያሳዝነው መሬቱ የተሸጠው ለሪል እስቴት ነው፡፡ በሌላ በኩል አዲስ አበባ ተራቆተች ብለን ችግኝ አፍልተን እንሰቃያለን፡፡ ያልተቀናጀ ስልትና ልማት ቀዳዳ በርሜል እንድንሞላ አድርጎናል፡፡

የየካ ደን ለሪል ስቴት ሲባል የሚጨፈጨፍበት አግባብ የእብድ ውሳኔ ነው፡፡ ለጥቂት ቅንጡ ሰዎች የተራራ ላይ ኑሮ ከተማዋ ካላት ጥቂት ነባር ሳንባ አንዱን መጨፍለቅ ተገቢ አይደለም፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top