Connect with us

ኢትዮጵያ የአባይ ወንዝ ከአፍሪካ አገራት ጋር ዲፕሎማሲዋን ማጠናከር አለባት

ኢትዮጵያ የአባይ ወንዝ ተጠቃሚነቷን ለማረጋገጥ ከአፍሪካ አገራት ጋር ዲፕሎማሲዋን ማጠናከር አለባት
Photo: ENA

ፓለቲካ

ኢትዮጵያ የአባይ ወንዝ ከአፍሪካ አገራት ጋር ዲፕሎማሲዋን ማጠናከር አለባት

“የህዳሴው ግድብ ጉዳይ በቀዳሚነት የሚመለከተው ሶስቱን ሃገራት (ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን) ሲያልፍም አፍሪካዊያንን ነው” ያሉት ፕሮፌሰሩ ኢትዮጵያ የምትከተለው ፍትሃዊ ተጠቃሚነት በብዙ የአፍሪካ ሃገራት የሚደገፍ ነው ብለዋል።

የሶስቱን ሃገራት ጉዳይ ከአፍሪካውያን ውጭ አሳልፎ መስጠት ከፍትሃዊነቱ ይልቅ ጉዳዩ ለፖለቲካ አጀንዳነት እንዲውል ያደርገዋል ነው ያሉት።

ከሶስቱ ሃገራት ባለፈ ለቀጠናውና ለአህጉሪቱ ሰላም እንደማይጠቅም ተናግረው ኢትዮጵያ ጉዳዩ በቀጥታ ከሚመለከታቸው አፍሪካዊያን ጋር የዲፕሎማሲ ትስስሯን ልታጠናክር ይገባታል ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የሃገር ውስጥ ፖለቲካውን በማስተካከል በብሄራዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ ያለውን አንድነት ማጠናከር ያስፍልጋል ብለዋል።

በሃገር ውስጥ ባሉ ፖለቲከኞች መካከል ምንም አይነት የሃሳብ ልዩነት መንሸራሸሩ የዴሞክራሲ መገለጫ ቢሆንም ህዝብን፣ ሃገርንና ሉአላዊነትን አደጋ ላይ በሚጥል ጉዳይ ላይ ግን ልዩነት መኖር የለበትም ብለዋል።

የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ኦባንግ ሜቶ እንዳሉትም በአባይ ወንዝ አጠቃቀም ዙሪያ የኢትዮጵያን ተጠቃሚነት ያላካተተ የቅኝ ገዥዎች ስምምነት በየትኛውም መመዘኛ ተቀባይነት የለውም።

በ21ኛው ክፍለ ዘመን እንዲህ አይነት ተግባራትን ለማስቀጠል መሞከርም ከሰብአዊነት ያለፈና ኢትዮጵያ የማትቀበለው መሆኑን አብራርተዋል።

ግድቡ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን እንደመሆኑ በተጠቃሚነት ጉዳይ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዜጋ በጥብቅ የሚመለከተው መሆኑንም ገልጸዋል።

ከ60 በመቶ በላይ ዜጎቿ በጨለማ ውስጥ የሚኖሩባት ኢትዮጵያ ግድቡን እየገነባችው ያለው የኤሌክትሪክ ሃይል ለማመንጨት መሆኑ ይታወቃል።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አፈፃፀም አሁን ላይ 73 ነጥብ 7 በመቶ ደርሷል።

Continue Reading
Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top