Connect with us

ሱዳን የኢትዮጵያ ታጣቂዎች ወታደራዊ መኮንኔን ገደሉ አለች

ሱዳን የኢትዮጵያ ታጣቂዎች ወታደራዊ መኮንኔን ገደሉ አለች
Photo: Facebook

ፓለቲካ

ሱዳን የኢትዮጵያ ታጣቂዎች ወታደራዊ መኮንኔን ገደሉ አለች

ሱዳን የኢትዮጵያ ታጣቂዎች ወታደራዊ መኮንኔን ገደሉ አለች
(ታምሩ ገዳ/ህብር ራዲዮ)

በኡትዮ ሱዳን ድንበር ላይ በኢትዮጵያ ታጣቂዎች እና በሱዳን የመከላከያ አባላት መካከል በተካሄደ የድንበር ላይ ግጭት ሳቢያ አንድ የሱዳን መንግስት የጦር መኮንን መሞታቸውን፣ በርካታዎች መቁሰላቸውን እና ንብረት መወረሱን ካርቱም አስታወቀች።

የሱዳን የዜና አገልግሎት ሱናአ (SUNA) ዋቢ በማድረግ ሮይተርስ ከካርቱም፣ ሱዳን እንደዘገበው ” በምስራቅ የአገሪቱ ክፍል አል ገዳሪፍ ተብሎ በሚጠራው የእርሻ ፕሮጀክት ዘልቀው የገቡ እና ባራካት ኖሪያት በተባለው የወታደራዊ ካምፕ ከሚገኙ የሱዳን ወታደሮች ጋር የተጋጩት የኢትዮጵያ ታጣቂዎች አንድ የሱዳን ወታደራዊ መኮንንገድለዋል፣ በርካታ ወታደሮችን አቆስለዋል”ብሏል

የቱርክ የዜና ወኪል አናዶሉ በበኩሉ የሱዳን ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣን የሆኑት ብርጋዴር ጄ/ን አሚር መሀመድ አል ሀሰን ያወጡት መግለጫን ጠቅሶ “በኢትዮጵያ ወታደሮች የሚታገዙ ታጣቂዎች ገዳሪፍ አካባቢ ካለፈው ግንቦት 26,2020 እኤአ ጀምሮ በመጋጨት ላይ ናቸው፣ ታጣቂዎቹ በበርካታ ቦታዎች ላይ ጥቃት አድርሰዋል፣ የሱዳኖች ንብረቶችንም ወርሰዋል፣ አንድ የወታደራዊ መኮንን ሱሞቱ፣ ስድስት ያህል ቆስለዋል፣ ሲቪሎችም ላይ ጉዳት ደርሷል” በማለት የወነጀሉት የሰዳኑ ከፍተኛ ብርጋዴር ጄ/ል አሚር “ሰራዊታችን የመልሶ ማጥቃት አድርጎባቸዋል” ሲሉ አስተያየት መስጠታቸውን አናዶሉ አክሎ ገልጿል።

ኢትዮጵያ እና ሱዳን ለዘመናት ያልተቋጨ የድንበር ይገባኛል ጥያቄ ያላቸው መሆኑ አይዘነጋም። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እገዝ እንዳላቸው በሱዳን በኩል ክስ ለቀረበው የኢትዮጵያ ታጣቂዎች ዙሪያ እስከአሁን ድረስ አግባብነት ካለው የኢትዮጵያ መንግስት በኩል የቀረበ ምንም አስተያየት የለም።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top