Connect with us

ከኒዮሊበራሊስት ተላላኪነት ወደ አብዮታዊ ድሞክራትነት

ከኒዮሊበራሊስት ተላላኪነት ወደ አብዮታዊ ድሞክራትነት
Photo: EPA

ፓለቲካ

ከኒዮሊበራሊስት ተላላኪነት ወደ አብዮታዊ ድሞክራትነት

ከኒዮሊበራሊስት ተላላኪነት ወደ አብዮታዊ ድሞክራትነት
የጓድ አምነስቲ ወቅታዊ አቋም!
(ታዬ ደንደአ የኦሮሚያ ብልፅግና ከፍተኛ አመራር አባል)

ባለፉት ሁለት ዓመታት በኢትዮጵያ ሰበአዊ መብቶች መጣሳቸዉ አይካድም። ህግን ከማስከበር አንፃር በመንግስት በኩል ውስንነቶች ቢኖሩም የወንጀሉ ዋና ተዋናይ ግን ወያኔ ነበር። ወያኔ ወንጀሉን ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ የግድያ ሙከራ ይጀምራል።

የብሔርና የሀይማኖት ግጭት ቀስቅሶ ህይወት እና ንብረት በማጥፋት ይቀጥላል። ተማሪዎችን እርስ በእርስ እስከማባላት ይደርሳል። ዋናዉ ግቡ የሩዋንዳን የዘር ጭፍጨፋ በኢትዮጵያ መድገም እንደሆነ ይታወቃል። ለዓላማዉ ስኬት በርካታ ድራማዎችን ሠርቷል።

ጫወታዉ ደግሞ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች መሀከል ይከወናል። በሁለቱም ክልሎች ፅንፈኝነት እንድነግስ ይደረጋል። ለጫወታዉ ድምቀት ኦነግ-ሸኔን (ጀዋርን) እና አብን (እስክንድርን) አሰልጥኖ ያጫውታል። በዚህ መሀል ብዙ የህይወት፣ የአካልና የንብረት ጥፋቶችን አድርሷል።

የሚሰራቸዉን ወንጀሎች ደግሞ በመደበኛና በማህበራዊ ሚዲያ መንግስት ላይ ለማላከክ ጥሯል። አምነስቲ ደግሞ የወያኔን እና የባለሟሎቹን ፕሮፓጋንዳ “የዓመቱ ሪፖርት” ብሎ በመፃፍ አስነብቧል።

በዚህ የተነሳ ወያኔ እና አምነስቲ ታርቋል። ወያኔም አምነስቲን ከኒዮሊብራሊስት ተላላኪነት ወደ ጓድ አብዮታዊ ዴሞክራት ቀይሯል። የማይለወጥ የለማ!

እዉነቱ ግን ይታወቃል። መንግስት ሰበአዊ መብቶችን ለማስከር ከነውስንነቱ ብዙ ሰርቷል። የወያኔን ሴራ በማክሸፍ ኢትዮጵያ እንደ ሊብያ ወይም እንደሩዋንዳ እንዳትሆን በማድረጉ ሊወገዝ ሳይሆን ሊመሰገን ይገባል!

አምነስቲ ግን ለምን የሌለ ድራማ ያወራል? አይ ጓድ አምነስቲ! በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ወያኔ ሆኖ ቁጭ! ሀምሳ ገፅ ፅፎ..ፅፎ..ፅፎ ምንም ሳይፅፍ ጭጭ! የሰብአዊ መብት ተከራካሪ!

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top