Connect with us

በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ወጣት ተማሪ ህይወቷ አልፎ ተገኘ

በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪ የነበረችው ሃይማኖት በዳዳ የተሰኘች ወጣት ህይወቷ አልፎ ተገኘ
Photo: Social media

ህግና ስርዓት

በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ወጣት ተማሪ ህይወቷ አልፎ ተገኘ

በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪ የነበረችው ሃይማኖት በዳዳ የተሰኘች ወጣት ህይወቷ አልፎ ተገኘ

ፖሊስ ከወንጀሉ ጋር በተያያዘ አራት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ማዋሉን ገልጿል።

የ27 አመት ወጣቷ ግንቦት 17 2012 በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 4ኛ ፎቅ ላይ በምትማርበት ቤተ ሙከራ እኩለ ቀን ላይ ሞታ መገኘቷን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የግድያ ወንጀሎች ዘርፍ ዳይሬክተር ለኢቲቪ ገልጿል።

በዚሁ ቀን በእለተ ሰኞ እንደወጣች በመቅረቷ ጠፍታለች የሚል ጥቆማ የደረሰው የኮሚሽኑ የምርመራ ቡድን በምትማርበት የቤተ ሙከራ ክፍል ትናንት ግንቦት 18 ከቀኑ 11 ሰአት ተኩል አቅንቶ ሟች የምትማርበት ክፍል የተቆለፈ የነበረ በመሆኑ ሰብሮ እንደገባ የሟች አስክሬንን ማግኘቱን ገልጿል።

የምርመራ ቡድኑ በሰአቱ ሟች አንገቷና ደረቷ ላይ በስለት ተወግታ መሞቷን ቢመለከትም ለተጨማሪ ምርመራ አስክሬኗን ለቅዱስ ዻውሎስ ሚሊኒየም ኮሌጀ መላኩን ከዳይሬክቶሬቱ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

የምርመራ ቡድኑ ከሆስፒታል የሚወጣውን ምርመራ ከመጠበቅ ጎን ለጎን በአሁኑ ጊዜ የቴክኒክና የታክቲክ ማስረጃ እያሰባሰበ መሆኑን ገልጿል።

የዚህን ተጨማሪ የምርመራ ውጤት ዳይሬክቶሬቱ ለህዝቡ እንደሚያሳውቅም ገልጿል።

ምንጭ:- ኢቲቪ

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top