Connect with us

ሕገ መንግሥትና ምርጫ

ሕገ መንግሥትና ምርጫ

ህግና ስርዓት

ሕገ መንግሥትና ምርጫ

ሕገ መንግሥትና ምርጫ
(ኘሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም)
ግንቦት 2012

የመገለባበጥ ጨዋታ ውስጥ የሚገለባበጡት ሰዎች እርስበርሳቸው ሲተያዩ መገለባበጣቸውን ይመለከታሉ፤ በመመልከትም አእምሮአቸው አዙሪት ውስጥ ይገባል፤ ከመገለባበጡ ተመልሰው ሲቆሙ ወይም ሲያርፉ አዙሪቱ አይለቃቸውም፤ ዛሬም በመገለባበጥ ላይ ናቸው፤ ስለዚህ ከእነሱ ቁም-ነገር ለማግኘት መሞከር ሕዝብን ለማታለል ካልሆነ ሌላ ፋይዳ የለውም፡፡

በመሠረቱ የሚደንቀኝ ግን ሕግን ለመጣስና ሕግን ለማስጣስ መሣሪያ የነበሩ ሰዎች ተሰብስበው ስለሕገ መንግሥት መኖርና አለመኖር ሲከራከሩ ማየቱ ነው፤ አንዳንድ የላቀ አእምሮ ያላቸው ሰዎችም እዚህ ዶሮ ማታ ዶሮ ማታ ጨዋታ ውስጥ መሳተፋቸው ነው፤ የግብዞችን ውይይት ስሰማ ረስቼው የነበረውን የሮማውያን ገዢ ማርከስ ኦሪልየስን ጽሑፍ አስታወሰኝ፤ ከሞት የሚያመልጥ የለም፤ የሕገ መንግሥቱ መሀንዲስ ሲፈልገው ፕሬዚደንት፣ ሲፈልገው ጠቅላይ ሚኒስትር የሚሆነው፣ ሲፈልገው ይህን አንቀጽ፣ ሲፈልገው ይህኛውን አንቀጽ ከሕገ መንግሥቱ በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የሚሰርዘው ዛሬ የለም፡፡

እግዚአብሔር ከመሸጦነትና ከኮረና ይጠብቀን!

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top