Connect with us

ብልፅግና ~ ህወሓትን በድጋሚ አስጠነቀቀ

ብልፅግና ~ ህወሓትን በድጋሚ አስጠነቀቀ
Photo: Facebook

ፓለቲካ

ብልፅግና ~ ህወሓትን በድጋሚ አስጠነቀቀ

የትግራይ ክልላዊ መንግስት በተናጠል ምርጫ እንደሚያካሂድ የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ሰሞኑን መናገራቸውን ተከትሎ የብልፅግና ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሐላፊ አቶ አወሉ አብዲ መንግሥት አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

የፌደራሉን መንግስት የሚመራው የብልፅግና ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሐላፊ አቶ አወሉ አብዲ እንዳሉት የትግራይ ክልል መንግስት በክልሉ ምርጫ ማድረግ አይችልም ፤ ካደረገም መንግሥት አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል ሲሉ የፓርቲያቸውን አቋም አንፀባርቀዋል።

ዶ/ር ደብረፅዮን በመግለጫቸው ምርጫውን እናካሂዳለን ማለታቸውን ተከትሎ ቀደም ሲል ጀምሮ ከፌደራል መንግሥት እየተሰማ ያለው ተገቢነት የሌለው ነው ካሉ በኃላ ስልጣን ላይ መቆየት የለብንም፤ ስልጣናችንን በህዝብ ለሚመረጥ አካል እናስረክባለን በማለታችን መደገፍ እንጂ ከዚህ ውጭ አላስፈላጊ ነገሮች ማለት ስህተት ነው ማለታቸው ተሰምቷል።

በሌላ በኩል በመቀለ ከተማ በህወሓት አሰባሳቢነት የተመሰረተውና ራሱን የፌደራሊስት ሀይሎች ጥምረት ብሎ የሚጠራው ስብስብ ህወሓት በክልሌ ምርጫ አደርጋለሁ ማለቷ የጥምረቱን ህገደንብ ያላከበረ ነው በማለት ትላንት በአዲስአበባ ባካሄደው ስብሰባ አውግዟል። ጥምረቱ ከኮሮና ቫይረስ ስጋት ጋር ተያይዞ አገራዊ ምርጫ እንዲራዘም በገዥው ፓርቲ በኩል የቀረበውን ጥያቄ እንደሚደግፍም አረጋግጧል።

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top