የግብጽ አቋም ፣ሴራ እና የአጋሮቿ ድጋፍ ሰሞኑን ግብፅ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በፃፈችው ደብዳቤ የግድቡን ሙሌት እንዲዘገይ ጥያቄ ማቅረቧ ይታወቃል፡፡ ግብጽ ለምክር ቤቱ በፃፈችው ደብዳቤ ኢትዮጲያ በቀጠናው አደጋ እንደ ደቀነች፣ ግድቡን ለብቻዋም ምንም አይነት ውሳኔ መወሰን እንደማትችል እና የግድቡንም ግንባታ የጀመረችው ማንንም ሳታማክር ነው በማለት ከሳለች፡፡
ከዚህም ባሻገር የግብፅ መከላከያ ሚንስትር እና የመከላከያ ኢታማዦር ሹም ጀነራል መሀመድ አህምድ ዛኪ የግብፅ ፕሬዚዳንት የቀኝ እጅ ሲሆኑ በአንድ መድረክ ማንኛውንም እርምጃ ፣ በማንኛውም ጊዜ እንወስዳለን ሲሉ መዛታቸውን ከግብጽ በሚስጢር የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
የግብፅ ሰራዊት ቺፍ ኦፍ ስታፍ ሌተናንት ጀነራል ፋሪድ ሂጋዚ ፣ የባህር ሀይሉ አዛዥ ሌተናንት ጀነራል ካሊድ ሀሰን ሰድ አህምድ እና ሌተናንት ጀነራል መሀመድ አባስ ሂላሚ ሀሰም በጋራ ምክክር ባደረጉበት ወቅት በማንኛውም መንገድ የገድቡን ሙሌት ማስቀረት እና ማሰናከል እናዳለባቸው በቅርቡ ባደረጉት የጋራ ስብሰባ ላይ ደምድመዋል፡፡ ግብፅ የግድቡን መሞላት ለማስቀረት የመጀመሪያ አማራጭ አድረጋ የወሰደችው ኢትዮጲያ በአለም አቀፉ ማህበረሰብ መገለል እንዲደርስባት እና ገድቡን ከመሙላት እንድትታቀብ ማድረግ ነው፡፡
ይህ ካልሆነ ግን ሌሎች አማራጮችን መጠቀም እንደሚገባም ወስናለች፡፡
ከእነዚህም ውስጥ በደቡብ ሱዳን በኩል ብሉ ናይል ግዛት በመጠጋት ወታደራዊ ጥቃት ለመውሰድ ወስነው የደቡብ ሱዳንን ይሁታ ለማግኘት ሙከራ እያደረገች ሲሆን ሱዳንንም በማግባባት መነሻ ቦታ ካገኘች ከሱዳን በመነሳት ግድቡን ለመምታት የመከላከያ መኮንኖች መዘጋጀት እንዳለባቸው ተወስኖ ወደ እንቅስቃሴ ተገብቷል፡፡ በሶማሌም በኩል ሙከራ ብታደርግም የሶማሌ መንግስት ግን ኢትዮጲያ የቀጠናውን ሰላም ከማስጠበቋም በላይ አልሻባብን እስከ ሶማሌ ድረስ ገብታ እየመታች በመሆኑ ከኢትዮጲያ ጋር ወደ መቃቃር መግባት እንደማትፈልግ አሳውቃለች፡፡
በሶስተኛ ደረጃ እንደ አማራጭ የተወሰደው የአፍሪካን አገራት ማግባባት እና የግብፅን አቋም እንዲደግፉ ማድረግ ሲሆን ይህንን ተልዕኮ ባለቤተነት ይዞ በመንቀሳቀስ ላይ ያለው ኮሎኔል አብዱል የተባለ የጦር መኮንን መኮንን ነው፡፡ በሌላ በኩል የኢትዮጲያን ዝርዝር ሁኔታ ለመከታተል የተመደበው የጦር መኮንን ብርጋዴር ጀነራል ኢስላም የሚባል ሲሆን የኢትዮጲያን ውስጣዊ ሁኔታ በዝርዝር እየተከታተለ አገራዊ ውስጣዊ ሁኔታችንን በመበርብር ግጭቶችን እና አገራዊ ቀውሶችን የመቀስቀስ ቁልፍ ስራው ነው፡፡ ይህንን የውስጥ ጉዳይ ዋነኛ አጋር እና መሳሪያ ሆና እንድታገልግል የተመረጠችው ህወሀት ናት፡፡ በዚህ ረገድ የአልሲሲ የቅርብ ሰው የሆነው ሜጀር ጀነራል አባስ ከማል የግድቡን እያንዳንዷን መረጃ ይዞ የሚከታተል ሲሆን በአካባቢው አገራት ላይ ጫና ለመፍጠር ሙከራ እያደረገ ነው፡፡
ይህ ጀነራል እንደ መሳሪያ የሚጠቀመው ጌታቸው አሰፋን ሲሆን ማንኛውንም መረጃ በጌታቸው አሰፋ በኩል እያገኘ ተንትኖ ለስራ ይጠቀምበታል፡፡ ጌታቸው አሰፋን ከጀነራል አባስ ጋር በማገናኘት ከፍተኛ ሚና በመጫወት ላይ ያለው ደግሞ በቀድሞው የሱዳን ፕሬዚዳንት አልበሽር ዘመን የሱዳን መኮንን የነበረው እና ከለውጡ በኋላ ሸሽቶ ግብፅ የገባው ጀነራል ሳላጎሽ የተባለ ሱዳናዊ ነው፡፡ ይህ ሰው ከጌታቸው አሰፋ በተጨማሪ ከህወሀት ቁልፍ አመራሮች ጋር የቅርብ ግንኙነት ያለው ሲሆን ለህወሀት ተልዕኮ በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ የግብፅ ጀነራሎች የከቪድ -19ኝን ቫይረስ በጅቡቲ በኩል ወደ ኢትዮጲያ በማስገባት ኢትዮጲያ በወረርሽኙ ክፉኛ እንድትጎዳ በማድረግ የግድቡን ሙሌት ማደነቃቀፍ እና ግድሙ ሳይሞላ የሚቀጥለውን ክረምት እንዲያልፍ ማድረግ የሚል ዕቅድም አዘጋጅተዋል፡፡
የኮሮና ቫይረስን ወደ ግደቡ ሰዎች በማዳረስ በስራ ላይ ያሉት ሰዎች ስራ እንዲያቆሙ እና የግድቡ ግንባታ እንዲዘገይ ወይም ባለሀብቶችን በማስፈራራት የግድቡን ሙሌት ማዘግየት የሚል እቅድም አዘጋጅተው በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው ከህወሀት በተለይም ከጌታቸው አሰፋ እና ጌታቸው ረዳ ጋር በጋራ በመስራት ላይ ሲሆኑ እነ ጌታቸው አሰፋ ግንባታው እንዲዘገይ እንዲሰሩ ተልዕኮ ተሰጥቷቸዋል (ጌታቸው ረዳ ከአሁን ቀደም ወደ ኬንያ እና ግብፅ በስውር ይመላለስ እንደነበረ በማህበራዊ ሚዲያው ሲገለፅ እንደነበረ ያስታውሷል)፡፡
ጃዋር መሀመድን እንደ መሳሪያ በመጠቀም አገሪቱን ወደማትወጣው ቀውስ ውስጥ ማስገባት ታቅዶበት እየተሰራ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የኦነጉ ዳውድ ኢብሳ ባለቤቱ ግብፅ የምትኖር ሲሆን ዳውድም ይመላለስ ስለነበር አንዱ ጠቃሚ ሰው ተደርጎ ተወስዶ እየተሰራበት ነው፡፡ ግብፆች ዳኦድ ኢብሳን ላሰቡት አላማ እሺ በማለት ያሳካለቸው ይሆን? አብረን የምናየው ነው::
ሌላው በሮመዳን የመጀመሪያ ሳምንት አካባቢ ሶስት ግፃዊያን ሱዳን ብሉ ናይል ክልል ሪሴሪስ በተባለ ሲንቀሳቀሱ በሱዳን መከላከያ ሰራዊት አማካኝነት በቁጥጥር ስራ ውለዋል፡፡ ግለሰቦቹም ጂ ፒ ኤስ (GPS) ይዘው የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ለምርምራ ወደ ካርቱም እንደ ተላኩ ከቀጠናው የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
(የብልፅግና ፓርቲ ፌቡ ገፅ)