Connect with us

በድሬደዋ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የተላለፉ ተቀጡ

በድሬደዋ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የተላለፉ ተቀጡ
Photo: Social media

ህግና ስርዓት

በድሬደዋ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የተላለፉ ተቀጡ

የተከሳሾች የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳዉ ሚያዚያ 18 ቀን 2012 አ.ም በድሬደዋ ከተማ ቀበሌ 04 በተለምደዉ ጋንዳቆሬ በሚባል አካባቢ የሚገኘዉ ግሎባል ሆቴል የተባለዉ የንግድ አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ሰዎችን ለበሽታዉ ተጋላጭ ሊያደርግ በሚችል መልኩ ሊያስተናግድ ከሚችለዉ አቅም ውጭ ከ100 ሰዎች በላይ በአዋጁ የተደነገገዉን ሁለት ሜትር በቂ እርቀት ባልጠበቀ ሁኔታ አገልግሎቶችን ሲሰጥ በመገኘቱ ተከሷል።

በተጨማሪም ዋርካ ባርና ሬስቶራንት የተባለዉ የንግድ አገልግሎት ሰጪ ድርጅትም በተመሳሳይ መልኩ በርካታ ቁጥር ላለዉ ሰዉ ያለ በቂ ርቀት ለኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ተጋላጭ በሚደረግ መልኩ ያልተፈቀደለትን የአልኮል መጠጥ አገልግሎት ጭምር ሲሰጥ በመገኘቱ የድርጅቱ ባለቤቶች በበቁጥጥር ስር ወለው የአስቸኳይ ግዜ አዋጁንና አዋጁን ለማስፈፀም የወጣዉን ደንብ በመተላለፋቸዉ በፈፀሙት ተግባር ምርመራቸዉ ተጣርቶ በፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ክስ ሊመሠረትባቸዉ ችሏል::

ጉዳዩን የተመለከተዉ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎትም ሚያዚያ 22 ቀን 2012 አ.ም ባስቻለዉ ችሎት የግሎባል ሬስቶራንት አቶ ሰለሞን እንዳለን በ15 ሺ ብር እንዲሁም ዋርካ ባርና ሬስቶራንት ባለቤት አቶ ሶፊኒያንስ አቦኒ በ32 ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኖባቸዋል::

በተመሳሳይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመተላለፍ ተፈራ ቦጋለ፣ ቢኒያም ከተማ እና ትዕግስት ተሰማ የተባሉት ጫት ሲያስቅሙና ሺሻ ሲያስጨሱ የነበሩት ተከሳሾች የቅጣት ዉሳኔ ተላለፈባቸዉል::

የፖሊስ የምርመራ መዝገብ እንደሚያስረዳዉ ሶስቱ ተከሳሽ ግለሰቦች በድሬደዋ ከተማ ቀበሌ 03 ኤም ኤ ጀርባና ነበርዋን ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ ሚያዚያ 13 ቀን 2012 አ.ም 11 ሰዎችን በጠባብ ክፍሉ ዉስጥ ለበሽታዉ ተጋላጭ ሊያደርግ በሚችል መልኩ ጫት ሲያስቅሙና ሺሻ ሲያስጨሱ በመገኘታቸዉ ነዉ በቁጥጥር ስር የዋሉት::

በዚህም የአስቸኳይ ግዜ አዋጁንና አዋጁን ለማስፈፀም የወጣዉን ደንብ በመተላለፋቸዉ በፈፀሙት ተግባር ምርመራቸዉ ተጣርቶ በፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ክስ ሊመሠረትባቸዉ ችሏል::

ጉዳዩን የተመለከተዉ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት ሚያዚያ 21 ቀን 2012 አ.ም በዋለዉ ችሎት ተከሳሾቹ እያንዳዳቸዉ በ2 ሺ 500 ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኖባቸዋል::

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top