Connect with us

ክብር ለአርበኞቻችን፤ እናንተ የከንባታ አባቶች ስለኢትዮጵያዊነት …

ክብር ለአርበኞቻችን፤ እናንተ የከንባታ አባቶች ስለኢትዮጵያዊነትና ስለ ሀገር ሉዓላዊነት
ከታሪኩ ጋር የተለጠፈው ፎቶ ከድህረ ገፅ የተገኘ የአባት አርበኞች ምስል ነው::

ባህልና ታሪክ

ክብር ለአርበኞቻችን፤ እናንተ የከንባታ አባቶች ስለኢትዮጵያዊነት …

ክብር ለአርበኞቻችን፤ እናንተ የከንባታ አባቶች ስለኢትዮጵያዊነትና ስለ ሀገር ሉዓላዊነት ለከፈላችሁት የአርበኝት ተጋድሎ በደም የተጻፈ ታሪክ አትማችኋልና እናመሰግናለን፡፡

ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም የአርበኞች ቀንን ምክንያት በማድረግ የአርበኛ አባቶቻችንን መልካም ገድል እያስታወሰ መዘከሩን ቀጥሏል፡፡ ጀግኖቹ የከንባታ አባቶች በማይጨው ጦርነት ስማቸውን በክብር የጻፉ ባለውለታዎች ናቸው ይለናል በተከታዩ ዘገባ፡፡ | ከሄኖክ ስዩም በድሬቲዩብ

“ጀግናውና ደፋሩ ደጃዝማች መሸሻ የከንባታውን ጦር እየመራ እንደቀዳሚ ጦር ከጦር ሰፈራችን መጀመሪያ ወጣ፡፡” ይኼንን የሚለን አዶልፍ ፓርለስካ ነው፡፡ እሱ የሀበሻን ድንቅ ጀብድ የጦር ሜዳ ውሎ ሲዘግብ ያኔ የከንባታ ጀግኖች የሰሩት ድንቅ ገድል ለትውልድ አኑሮታል፡፡

በዚያ ለሀገር በተከፈለ መስዋዕትነት ቀዳሚ ጦር ኾነው የወጡት የከንባታ አባቶች ስለ ሀገር ነጻነት ተዋድቀዋል፡፡ ድንቅ ነገር ሰርተዋል፡፡ ለትውልድ ነጻነት ህይወት የከፈሉ ጀግኖች ናቸው፡፡

መጋቢት 10 ቀን እስከ ቀኑ ማብቂያ ካላበቃው የአውሮፕላን ድብደባ ጋር ታግለው በተንቤን ጦርነት በጀግንነት የተዋደቁት የከንባታው ጦር መሪ ደጃዝማች መሸሻ ለሚወዷት ሀገራቸው በግሩም ጀግንነት በተዋጉበት አውደ ውጊያ መውደቃቸውን የማይጨው ዘመቹ ገብረወልድ እንግዳወርቅ የማይጨው ዘመቻና የጉዞውን ታሪክ በአስቀሩበት ማስታወሻ አኑረውልናል፡፡ ተክለ ጻዲቅ መኩሪያ ታላቁ የጦር ጀግና የጀብደኞቹ ተዋጊዎች የከንባታዎቹ መሪ ደጃች መሸሻ በተመቱ በአምስተኛው ቀን መጋቢት 15 ቀን ህይወታቸው ማለፉን አስፍረዋል፡፡

አዶልፍ ፓርለስካ መሪያቸውን ብቻ ሳይኾን ተከታዮቹን የከንባታ ልጆች ጀግኖችና ደፋሮች ሲል አወድሷቸዋል፡፡
የተንቤኑ ጦርነት እጅግ ከባድ ነበር፡፡ ከሀገር ልጅ ጋር በአንድ አውደ ውጊያ የተሰለፉት የከንባታ አባቶች ግን ታላቅ ታሪክ ሰሩበት፤ ትውልድ ሲያነበው የሚኖር ታሪክን በደም ጻፉበት፡፡

ከታሪኩ ጋር የለጠፈው ፎቶ ከድህረ ገፅ የተገኘ የአባት አርበኞች ምስል ነው።

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top