Connect with us

የትንሳኤ በዓል በጥንቃቀቄና ርቀትን ጠብቆ መከበር እንዳለበት የጤና ሚኒስትሯ አሳሰቡ

የትንሳኤ በዓል በጥንቃቀቄና ርቀትን ጠብቆ መከበር እንዳለበት የጤና ሚኒስትሯ አሳሰቡ
Photo Facebook

ጤና

የትንሳኤ በዓል በጥንቃቀቄና ርቀትን ጠብቆ መከበር እንዳለበት የጤና ሚኒስትሯ አሳሰቡ

የትንሳኤ በዓል በጥንቃቀቄና ርቀትን ጠብቆ መከበር እንዳለበት የጤና ሚኒስትሯ አሳሰቡ

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ የትንሳኤ በዓልን አስመልክቶ መልእክት አስተላልፈዋል።

ሚኒስትሯ በዚ መልዕክታቸውም፤ የትንሳኤ በዓልን ስናከብር እንደተለመደው በመሰባሰብ ሳይሆን ርቀት ጠብቆ ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ መሆን እንዳለበት ያሳሰቡት።

በዓሉን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን በመታገል ለሚያሳልፉ የጤና ባለሙያዎችና ሌሎች የህዝብ አገልግሎት መስጫ ሰራተኞችም ከወዲሁ ምስጋና አቅርበዋል።

የትንሳኤ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው እለት መሆኑን የተናገሩት ሚኒስትሯ፤ኢትዮጵያዊያን ከዚህ ቀደም ይህንን በዓል በአብሮነትና በመሰባሰብ ያሳልፋሉ ብለዋል።

ሆኖም አሁን ካለንበት ፈታኝ ወቅት አንጻር በዓሉን መሰባሰብና አብሮነት ማክበር እጅግ አደገኛ መሆኑንም አህጽኖት ሰጥተው ተናግረዋል።

በመሆኑም በዓሉን ስናከብር እራሳችንና ቤተሰባችንን ከኮሮናቫይረስ በመከላከል መሆን እንዳለበት መክረዋል።

በምግብ ዝግጅት ወቅት ያለምንም መዘናጋት ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግና ምግቦችን አብስሎ መብላት ይገባልም ብለዋል።

“አንዳችን ለሌላችን በማሰብ ይህንን አስቸጋሪ ወቅት ማለፍ አለብን” ሲሉም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ምንጭ – ኢዜአ

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top