Connect with us

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 2 ግለሰቦች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ተረጋገጠ

Photo Facebook

ዜና

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 2 ግለሰቦች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ተረጋገጠ

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 2 ግለሰቦች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ተረጋገጠ

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 286 ግለሰቦች መካከል ሁለቱ የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ይህን ተከትሎም በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 71 ደርሷል።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በላኩት መግለጫ፤ ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሁለቱም ግለሰቦች ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን አስታውቀዋል።

ሁለቱም ሴቶች ሲሆኑ፤ አንዷ የ24 ዓመት እድሜ ያላትና ከአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውሳኔ በፊት ከዱባይ የተመለሰች መሆኗን መግለጫው አመላክቷል።

ሌላኛዋ ግለሰብ የ35 ዓመት እድሜ ያላትና ከቱርክ ወደ ኢትዮጵያ መጥታ በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ክትትል ስታደርግ የነበረች ናት።

እስካሁን ባለው ሂደት በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ለ3 ሺህ 863 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ መከናወኑም በመግለጫው ተጠቁሟል።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው ግለሰቦች መካከል 56ቱ የህክምና ክትትል እያደረጉ ይገኛሉ።

አሁን ላይ በጽኑ ህሙማን ክፍል ክትትል የሚደረግላቸው ህሙማን አለመኖራቸውም በመግለጫው ተመላክቷል።

ቫይረሱ እንዳለባቸው ከተረጋጋጠባቸው ግለሰቦች መካከል ሶስት ሰዎች በቫይረሱ ህይወታቸው ማለፉ የሚታወስ ነው።

#ኢዜአ

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top