Connect with us

ሆሳአና-የዘንባባው በዓል ከአክሱም ጽዮን እስከ እንጦጦ

ሆሳአና-የዘንባባው በዓል ከአክሱም ጽዮን እስከ እንጦጦ፤
Photo Facebook

ባህልና ታሪክ

ሆሳአና-የዘንባባው በዓል ከአክሱም ጽዮን እስከ እንጦጦ

ሆሳአና-የዘንባባው በዓል ከአክሱም ጽዮን እስከ እንጦጦ፤
አቤቱ አሁን አድነን፤
****
(ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም የሆሳአና በዓል በዘንባባ ደምቆ መከበር ከጀመረባት የሀገራችን ታሪካዊት ስፍራ ከአክሱም ጽዮን እስከ እንጦጦ ሲል ቀኑንና ታሪኩን እንዲህ ዘግቦታል፡፡)
ከሄኖክ ስዩም በድሬ ቲዩብ

አዲስ አበባ ከዚያ ቀድሞ እንዲህ ያለ አከባበር አታውቅም ነበር፡፡ ወሩ መጋቢት ነው፡፡ ቀኑ ደግሞ 30፤ ፋሲካ ሊኾን አንድ ሳምንት ቀርቶታል፡፡ ዓመተ ምህረቱ 1898 ነው፡፡ እንጦጦ እንደ ርዕሰ አድባራት ወ ገዳማት አክሱም ጽዮን ባለ ሥርዓት ሆሳአናን ልታከብር ነው፡፡

ከአክሱም ጽዮን የመጡት አንድ መምህር የአከባበር ሥርዓቱን በተመለከተ ዝግጅት ሲያደርጉ ሥርዓቱን ለህጻናት ጭምር ሲያስተምሩ ሰንብተዋል፡፡ ሆሳአና የዘንባባ በዓል፡፡

አህያዋን የወከለችው የበቅሎ ግልገል የተነሳችሁ ከከንቲባ ወልደጻዲቅ ቤት ነው፡፡ በወርቅ ጥልፍ በተጠለፈ ሙካሽ አሸብርቃለች፡፡ ድባብ ተደብቦላታል፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ በአህያይቱ ውርንጭላ ጀርባ ላይ ኾኖ ሆሳአና እየተባለ በዝማሬ የተጓዘበትን የታሪክ አውድ እንጦጦ እንዲህ ባለው ውብ ሥርዓት ዘከረችው፡፡
መርስዔ ሐዘን ወልደ ቂርቆስ ትዝታቸውን ሲጽፉልን በዓሉ ንጉሠ ነገሥቱ ዳግማዊ ምኒልክና እቴጌ ጣይቱ በተገኙበት ሲከበር

ከዚያ ቀድሞ እንዲህ ያለው የአከባበር ሥርዓት በአክሱም እንጂ በሌላው ስፍራ ስላልነበረ እጅግ መደነቁንና ሰው መደሰቱን ነግረውናል፡፡

ከዚያ በኋላ የሆሳአና በዓል አከባበር እንዲህ ባለው ሥርዓት ቀጠለ፡፡ በሀገራችን ብዙ አካባቢዎችም የዘንባባው በዓል በዚህ ትውፊታዊ አከባበር ቀጠለ፡፡ ሆሳአና በዓል ብቻ ሳይኾን የታሪክን ክስተት ተከትሎም የከተማ ስም ኾነ፡፡

በ1889 ዓ.ም. የተመሰረተችውና ከባህር ወለል በላይ 2177 ሜትር ከፍታ ላይ ያረፈችው የሀድያዎች መዲና የሆሳዕና ዕለት ለአካባቢው ገዢ ተድርገው የተሾሙት ራስ አባተ በሆታ ታጅበው ገቡባት፡፡ ስሟንም ሆሳዕና አሏት፡፡
ሆሳዕና አሜን አሁን አድነን፤

ፎቶዎቹን ያገኘኋቸው የማኅበረ ደቂ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ትግራይ ገጽ ነው፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top