Connect with us

በአዲስ አበባ ከተማ የቤት ለቤት የኮሮናቫይረስ ምርመራ ሊጀመር ነው

በአዲስ አበባ ከተማ የቤት ለቤት የኮሮናቫይረስ ምርመራ ሊጀመር ነው
Photo Facebook

ዜና

በአዲስ አበባ ከተማ የቤት ለቤት የኮሮናቫይረስ ምርመራ ሊጀመር ነው

ምክትል ከንቲባው ታከለ ኡማ እንደገለጹት ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በአዲስ አበባ ሁሉም ወረዳዎች የኮሮናቫይረስ ምርመራ ይጀመራል።

ምርመራው ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ ተብለው ከተለዩ ወረዳዎች የሚጀምር መሆኑን ገልጸው በመዲናዋ 117ቱም ወረዳዎች ይከናወናል ብለዋል።

ለምርመራው ጡረታ ላይ የነበሩና በሞያው ልምድ ያላቸው ከ1 ሺህ 200 በላይ ሃኪሞች የመንግስትን ጥሪ ተቀብለው ካሉት ሃኪሞች ጋር ተጨማሪ ሃይል በመሆን ዝግጁ መሆናቸውንም ከንቲባው ገልጸዋል።

ከቤት ለቤት ምርመራው በተጨማሪ በሚቀጥለው ሳምንት ተማሪዎች በያሉበት ሆነው ትምህርት እንደሚጀምሩና የምገባ መርሃ ግብሩም እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

በተያዘው መርሃ ግብር መሰረት ከ7ኛ ክፍል በታች የሚማሩ ተማሪዎች ትምህርቱን በሬዲዮ የሚከታታሉ ይሆናል።

ከ7ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሚማሩ ተማሪዎች ደግሞ ትምህርታቸውን በፕላዝማ የሚከታተሉ ይሆናል።

በዚህ ሂደት ተማሪዎችና መምህራን የተለያዩ መረጃዎችን የሚለዋወጡበት የአሰራር ስርአትም መሰርጋቱ ተገልጿል።

የተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብርም በተለያዩ አካባቢዎች 1 ሺህ 200 ተማሪዎች የሚመገቡባቸው የምግብ ባንኮች ተዘጋጅተዋል፤ ለምግብ አቅርቦቱም 30 ሺህ ወጣቶች ዝግጁ ሆነዋል ተብሏል።

ምንጭ፡- ኢዜአ

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top