Connect with us

የዓለም የጤና ድርጅት የአፍሪካ ህብረት ሙሉ ድጋፍ አለው ሲሉ የህብረቱ ሊቀመንበር አስታወቁ

የዓለም የጤና ድርጅት የአፍሪካ ህብረት ሙሉ ድጋፍ አለው ሲሉ የህብረቱ ሊቀመንበር አስታወቁ
Photo: Social media

ማህበራዊ

የዓለም የጤና ድርጅት የአፍሪካ ህብረት ሙሉ ድጋፍ አለው ሲሉ የህብረቱ ሊቀመንበር አስታወቁ

የዓለም የጤና ድርጅት የአፍሪካ ህብረት ሙሉ ድጋፍ አለው ሲሉ የህብረቱ ሊቀመንበር ስሪል ራማፎሳ አስታወቁ።

የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም የኮሮናቫይርስ (ኮቪድ-19) ወረርሽን ለመከላከል እያደረጉት ያለውን ተግባርም አድንቀዋል።

ስሪል ራማፎሳ የኮሮናቫይረስ በብዙ ትውልዶች ከታዩ ድንገተኛ የጤና አደጋዎች በጣም የከፋና የቫይረሱ ስርጭት መቆጣጠር ገና ብዙ እንደሚቀረው በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።

”የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ያለ ምንም ጥርጥር የአኗኗር ዘይቤያችንን ቀይሮታል” ብለዋል።

ወረርሽኙ የጤና መሰረተ ልማቶች ላይ ፈተና እንደሆነና የኢኮኖሚ አቅርቦት ሰንሰለትን በመጉዳት የዓለም ኢኮኖሚ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እያሳደረ እንደሆነም ገልጸዋል።

ዓለም የኮሮናቫይረስ ይዞት ከመጣው ፈተና ጋር እየተዋጋ በሚገኝበት በዚህ ወቅት ይህንን የጋራ ጠላት የሆነ ወረርሽኝን ለማሸነፍ ትብብር፣ አንድነትና ቅንጅት እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።

”ከዚህ ተጨባጭ ሁኔታ በመነሳት የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የዓለም የጤና ቀውስ ያመጣውን ኮቪድ-19 ለመከላካል ላሳዩት ልዩ አመራር ያለኝን አድናቆት ዳግም ማረጋገጥ እፈልጋለሁ” ብለዋል።

Click to comment

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top