Connect with us

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የደነገገውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተንተርሶ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ማብራሪያ ሰጠ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የደነገገውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተንተርሶ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ማብራሪያ ሰጠ
Photo Facebook

ህግና ስርዓት

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የደነገገውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተንተርሶ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ማብራሪያ ሰጠ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የደነገገውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተንተርሶ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ማብራሪያ ሰጠ

ጠቅላይ አቃቤ ህግ በሰጠው ማብራሪያ እንዳለው፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተፈፃሚ በሚሆንበት ጊዜ ውስጥ ሁሉ የሚያስፈልጉት ክልከላዎች እና መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች ተለዋዋጭነት ሊኖራቸው ስለሚችል በየጊዜው ያለውን ሁኔታ በመገምገም እና ስለ ቫይረሱ ስርጭትም ሆነ ባህሪ የሚገኙ ሳይንሳዊ መረጃዎችን፣ የጤና ባለሞያዎችን ምክር ከግምት ውስጥ በማስገባት የመብት እገዳዎችን እና እርምጃዎችን ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል ብሏል፡፡

ይህን ለማድረግም ዝርዝር እና ቋሚ የመብት እገዳዎችን ከማውጣት ይልቅ እንደ አስፈላጊነቱ ተለዋዋጭ በሆነ ሁኔታ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ በማውጣት እገዳዎችና እርምጃዎችን እንዲደነግግ አዋጁ ስልጣን ይሰጠዋል ሲል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ተናግሯል፡፡

አዋጁ የተቀረፀው አስፈላጊ የሆኑ የመብት እገዳዎች እና እርምጃዎች ዝርዝር ሁኔታ ከጊዜ ጊዜ ከቦታ ቦታ ሊለዋወጥ እንደሚችል ታሳቢ በማድግ ተጨባጭ ሁኔታውን ከግምት በማስገባት አስፈላጊ እና ተመጣጣኝ የሆነ እገዳ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል አሰራር ለመዘርጋት ነው ብሏል፡፡

በወንጀል ህግ የተካተቱ አግባብነት ያላቸው የወንጀል ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው፣ ባስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሰረት የተደነገጉ የመብት እገዳዎችን እና እርምጃዎችን፣ የተሰጠን መመሪያ ወይም ትዕዛዝን ሆን ብሎ የጣሰ ማንኛውም ሰው እስከ 3 ዓመት በሚደርስ ቀላል እስራት ወይም ከ1 ሺ ብር እስከ 200 ሺህ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ሊያስቀጣ ይችላልም ተብሏል፡፡

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ከፀደቀበት ከዛሬ ጀምሮ ለ5 ወራት የፀና እንደሚሆን ጠቅላይ አቃቤ ህግ በሰጠው ማብራሪያ ተናግሯል፡፡

(ሸገር ራዲዮ)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top