Connect with us

ሕግ የሚተላለፉ 5 ሺ ብር ይቀጣሉ፣ የአሽከርካሪው መንጃ ፈቃድ ይታገዳል

ሕግ የሚተላለፉ 5 ሺ ብር ይቀጣሉ፣ የአሽከርካሪው መንጃ ፈቃድ ይታገዳል
Photo Facebook

ህግና ስርዓት

ሕግ የሚተላለፉ 5 ሺ ብር ይቀጣሉ፣ የአሽከርካሪው መንጃ ፈቃድ ይታገዳል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ አቶ ስጦታው አካለ በታክሲዎች እና ብዙሃን ትራንስፖርት የተሳፋሪ ቁጥር ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ ተሸከርካሪዎች የተሳፋሪ ቁጥርን በግማሽ መቀነስ የሚያስችል ውሳኔ ተላልፏል፡፡

በዚህም ታክሲዎች ከመደበኛ የመጫን አቅማቸው በግማሽ ቀንሰው እንዲጭኑ ውሳኔ የተላለፈ ሲሆን፥ 12 ሰው የመጫን አቅም ያለው ሚኒባስ ታክሲ 6 ሰው ብቻ እንዲጭኑ ተደርጓል፡፡

ሌሎች ተጨማሪ ወንበር ያላቸው እንደ ዶልፊን ታክሲዎች እንደወንበራቸው አቅም በግማሽ ቀንሰው ይጭናሉ፡፡
በሃይገር ባስ የተሳፋሪ ቁጥር በወንበር ልኩ በግማሽ ብቻ እንዲጭኑ የተደረገ ሲሆን፥ 14 ሰው ብቻ እንዲጭኑ ውሳኔ ተላልፏል፡፡

አንበሳ የከተማ አውቶቡስ እና ሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት አውቶቡሶች 40 ሰው ይጭን የነበረ መደበኛ አውቶቡስ 30 ሰው ብቻ የሚጭኑ ይሆናል፡፡

ረጃጅሞቹ የተማሪ አውቶቡሶች 30 ሰው ብቻ እና አጫጭሮቹ የተማሪ አውቶቡሶች 20 ሰው ብቻ እንዲጭኑ፤ እንዲሁም ደብል ዴከር አውቶቡሶች 50 ሰው ብቻ እንዲጭን ተወስኗል፡፡

በመሆኑም ከዛሬ መጋቢት 29 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በቀጣይ መመሪያ እስኪሰጥ ድረስ ታክሲም ሆነ ሃይገር አውቶቡስ ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት በፊት እና ከምሽቱ 2:00 ሰዓት በኋላ አገልግሎት እንዳይሰጥ ተደርጓል፡፡

በአንጻሩ አንበሳ እና ሸገር አውቶቡሶች በተለመደው የአገልግሎት መስጫ ሰዓታቸው አገልግሎት የሚቀጥሉ ይሆናል፡፡

ታክሲዎችና ሃይገር አውቶቡሶች የመጫን አቅማቸው ወደ መደበኛው እስኪመለስ ቀደም ሲል የነበረው ታሪፍ በእጥፍ አድጎ ተሳፋሪዎች እንዲከፍሉ ተደርጓል ፡፡

የአንበሳ እና የሸገር አውቶቡሶች ታሪፍ በነበረበት የሚቀጥል ሆኖ መንግስት በሚያደርገው ድጎማ እንዲሸፈን ይደረጋል፡፡

ማንኛውም ከተፈቀደው ሰው በላይ ጭኖና ከተፈቀደው ሰዓት ውጭ ሲሰራ የተገኘ ታክሲም ሆነ የሃይገር አውቶቡስ ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር) ይቀጣል፡፡

በተጨማሪም የአሽከርካሪው መንጃ ፈቃድ እስከመጨረሻው እንዲታገድ በማድረግ በሌሎች የሀገሪቱ ህጎች ተጠያቂ የሚደረጉም ይሆናል ተብሏል፡፡(የአ/አ ኘረስ ሴክረቴሪያት)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top