Connect with us

“በሽታው ገዳማትንና የአብነት ትምህርት ቤቶችን እንዳያጠቃ እየተሠራ ነው” ማኅበረ ቅዱሳን

"በሽታው ገዳማትንና የአብነት ትምህርት ቤቶችን እንዳያጠቃ እየተሠራ ነው" ማኅበረ ቅዱሳን
Photo Facebook

ዜና

“በሽታው ገዳማትንና የአብነት ትምህርት ቤቶችን እንዳያጠቃ እየተሠራ ነው” ማኅበረ ቅዱሳን

የኮሮና ቫይረስን ስርጭት ለመግታት በማኅበረ ቅዱሳን የተቋቋመው ግብረ ኃይል እስከ ወረዳ ድረስ በመደራጀት በሽታው ገዳማትንና የአብነት ትምህርት ቤቶችን እንዳያጠቃ እየሠራ መሆኑን አስታወቀ።

ኮቪዲ-19 ኮሮና ቫይረስን ስርጭት ለመግታት የሚያስችል ግንዛቤ ለመፍጠር የተቋቋመው ግብረ ኃይል እስከ ወረዳ ማእከልና አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ድረስ ተደራጅቶ እንዲሠራ የማሳወቅ፣ የማስተማር የማንቃት ተግባሩን ማከናወን መጀመሩን ገልጧል።

ግብረ ኃይሉ በትናንትናው ዕለት ለማእከላት ማስተባባሪያዎች በሚያገለግሉባቸው ማእከላት ሆነው በመስኮተ ትዕይንት (pal talk) ሥልጠና መስጠቱን የገለጠው በማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢና ዋና ጸሐፊ የሚመራው ግብረ ኃይሉ ሥልጠናው በሕክምና ባለሙያዎች መሰጠቱን አስታውቋል።

ሥልጠናው ሁለት መልክ እንደነበረው የገለጠው ግብረ ኃይሉ የመጀመሪያው ስለ ኮሮና ቫይረስ ግንዛቤ መፍጠር ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በቀጣይ መከናወን ስላለባቸው ተግባራት ተግባርና ኃላፊነት የሚሰጥ መሆኑን ገልጧል።

በቀጣይም ቅዱስ ሲኖዶስ በሚሰጠው መመሪያና መንግሥት በሚያወጣው አቅጣጫ መሠረት በአብነት ትምህርት ቤቶች፣ በገዳማትና አድባራት፣ በጸበል ቦታዎችና በሌሎችን ቦታዎች በየአካባቢው በመንግሥትና በቤተ ክህነት ከተቋቋሙ ግብረ ኃይሎች ጋር በመተባበር “ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ሕይወት ለመታደግ የሚያስችሉ ተግባራትን” ለማከናወን አቅጣጫ መቀመጡን አስገንዝቧል።

ግብረ ኃይሉ በሥሩ ሦስት ንዑሳን ኮሚቴዎች ያሉት ሲሆን እነዚህም ሚዲያና ሕዝብ ግንኙነት፣ በሽታውን የመከላከል ቅድመ ዝግጅትና መቋቋም(crises preparedness and management)እና ግብአት አሰባሳቢና ስርጭት መሆናቸውን ገልጦ የሰውን ልጅ ለመርዳት ለታሰበው የተቀደሰ ተግባር ተባብረው ለመሥራት ፈቃደኛ ከሆኑ አካላት ጋር ተባብሮና ተናቦ እንደሚሠራም አስታውቋል።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top