Connect with us

በኮሮና ምክኒያት ረዥም ሰዓትዎን በቤት ውስጥ ሲያሳልፉ ብቸኝነትንና የድብርትን እንዴት ማስወገድ ይቻላል?

በኮሮና ምክኒያት ረዥም ሰዓትዎን በቤት ውስጥ ሲያሳልፉ ብቸኝነትና የድብርትን እንዴት ማስወገድ ይቻላል?
GETTY IMAGES/MAPODILE

ነፃ ሃሳብ

በኮሮና ምክኒያት ረዥም ሰዓትዎን በቤት ውስጥ ሲያሳልፉ ብቸኝነትንና የድብርትን እንዴት ማስወገድ ይቻላል?

በኮቪድ-19 ምክንያት ካልተፈለጉ እንቅስቃሴዎች ተቆጥበው ረዥም ሰዓት በቤት ውስጥ ማሳለፍ በሽታውን ለመከላከል ከሚመከሩ ተግባራት አንዱ ነው። እንዲህ ያለው ወቅት ብዙ ጊዜ ቤት ውስጥ ማሳለፍ ላለመዱ ሰዎች ፈታኝ ሊሆን ይችላል። ከተለመዱ ተግባራት ብሎም ከማህበራዊ ግንኙነቶቹ የተገለለ ሠው የድብርትና የብቸኝነት ስሜት ሊሰማው ይችላል፡፡

ይሁን እንጂ ውሳኔው የራስንና የማህበረሰብን ጤና ለመጠበቅ የሚረዳ የሚያግዝ በመሆኑ ሁኔታዎች እስኪስተካከሉ ድረስ ተቋቁሞ ማለፍ ይገባል፡፡ ታዲያ በእነዚህ ጊዜያቶች ውስጥ ሊፈጠሩ የሚችሉ የድብርት ስሜቶችን እንዴት ማስወገድ ይቻላል? ከተለያዮ ድረ ገፆች ያገኘናቸውን ጠቃሚ ሀሳቦች እናካፍላችሁ።

በቤት ውስጥ ረዥም ሰዓት በምናሳልፍበት ጊዜ የድብርትና የመሰላቸት ስሜት አንዳይፈጠር ይረዳሉ ተብለው ተደጋግመው ከተገለፁት ተግባራት መካከል :

1.ከጓደኞች ጋር መደዋወል፣ የፅሁፍ መልክት መላላክ፣ ማህበራዊ ሚዲያን መጠቀም

ከጓደኞች ጋር ዘመኑ ያፈራውን ቴክኖሎጂ በመጠቀም መገናኘት ብቸኝነት ወይም ድብርትን ለመቀነስ ይረዳል፡፡ እንደ ቴሌግራም፣ዋትስ አፕ፣ እስካይፒ ያሉ ቴክኖሎጂዋች በመጠቀም ከወዳጅ ዘመድ ጋር መገናኘትና ሀሳብን መጋራት፤ የቪዲዮ ዉይይቶችን በእነዚህ ቴክኖሎጂዎች ማድረግ ግዜያችንን ያለ ድብርት ለማሳለፍ ይግዛል፡፡

2.መፅሐፍ ማንበብ

መንፈሳዊም ሆነ አለማዊ መፅሀፍትን ማንበብ ከድብርት ስሜት ከመገላገሉ በተጨማሪ ነገ ማህበረሰቡ ዉስጥ ስንቀላቀል ለህይወት መመሪያ የሚሆኑ መልካም ነገሮችን ያቀብሉናል፡፡ ማን ያውቃል ራሳችንንም በእነዚህ መፃህፍት ውስጥ ልናገኝ እንችላለን፡፡

3.ቤትን ማዘጋጀትና ማፅዳት

ከዚህ በፊት በህይወት ሩጫ ላይ ሆነን ልብ ያላልናቸው አላስፈላጊ የሆኑ እቃዎች ባንድ ላይ ተከማችተዎል? ይህ ጊዜ እነዚህን ለማሠናዳት ጥሩ እድል ይሠጠናል፡፡ እቃዎቻችንን ለይተን ለማዘጋጀትና ለማፅዳት እንዲሁም የቤት እቃዎቻችንን አቀማመጥ ለመቀየር በቂ ይህ ጊዜ አመች ዕድል ይፈጥርልናል፡፡ እንዲህ ያሉ ጠቃሚ ተግባራትን እየከዎን በሌላ በኩል ደግሞ ድብርትንም ደና ሠንብት ማለት እንችላለን፡፡

4.ምግብ ማብሠል

ምግብ ማብሠል ጥበብ ነው ፈጠራንም ይጠይቃል፡፡ እቤት ውስጥ በምናሳልፍበት ጊዜ ዉስጥ የተለያዩ ምግቦችን ማብሠልና የራሣችንን ፈጠራ ማከል ከድብርት ይገላግላል ሲሉ ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡

5.የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ

በቤት ውስጥ ቀለል ያሉ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ሠውነታችን ዘና እንዲል ከማድረጉ በተጨማሪ እንደ ጥሩ ጊዜ ማሣለፊያ ይጠቅመናል፡፡

6.ፊልሞች ማየትና፣ ዘፈኖችን ማዳመጥ

ፊልሞች ማየትና፣ ዘፈኖችን ማዳመጥ ሠውነታችንን ከማዝናናቱም በተጨማሪ መንፈሳችን እንዲታደስ በማድረግ ረገድ ትልቅ ሚና ይጫዎታሉ፡፡ እንደ ምርጫዎ የመንፈሳዊ መዝሙሮችን ማዳመጥም የተሻለ ጥንካሬን ያጎናፅፋል። ስለዚህ እነዚህን መዝናኛዎች እንደ ጥሩ አማራጭ በመጠቀም በቤት ውስጥ ስናሳልፍ ሊኖር የሚችል ድብርትና የብቼኝነት ስሜትን መቀነስ ብሎም ማስዎገድ ይቻላል፡፡

እነዚህን የመሳሰሉ ነገሮችን በማድረግ ድብርትና ብቸኝነትን መቅረፍ ይቻላል፡፡ እነዚህንም 5 ነገሮች በአንድ ቀን ማድረግ ይቻላል፡፡ ለምሳሌ ጠዋት ከእንቅልፋችን ተነስተን ለተወሠኑ ሠአታት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ቀጥሎ ምግብ ማብሠል ከዛም ቤት ማደራጀት ከድካም አረፍ ብለን ደግሞ መፀሀፍትን ማንበብ፡፡ ከዚያም፡ ከጓደኞች ጋር በስልክ ማዉራት ጊዜው ሳይሰለቸንና ሳያስጨንቀን እንዲያልፍ ይረዳናል፡፡

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top