Connect with us

በኢትዮጵያ ያለውን በረሃ አንበጣ ለመከላከል የአውሮፕላን ድጋፍ ተደረገ

በኢትዮጵያ ያለውን በረሃ አንበጣ ለመከላከል የአውሮፕላን ድጋፍ ተደረገ
Photo: Facebook

ዜና

በኢትዮጵያ ያለውን በረሃ አንበጣ ለመከላከል የአውሮፕላን ድጋፍ ተደረገ

የአለም የምግብ ድርጀት /FAO/ በኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተውን የበረሃ አንበጣ ለመከላከል የተባይ መርጫ አውሮፕላን ድጋፍ አደረገ፡፡

በርክክቡ ወቅት ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የግብርና ሚኒስትር ዴኤታው ዶ/ር ካባ ኡርጌሳ እንደገለጹት መነሻውን ከየመንና ሱማልያ አገራት አድርጎ ወደ ኢትዮጵያ የገባውን የበረሃ አንበጣ የመከላከል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

ይህንን ስራ ለማገዝ ደግሞ የአለም የምግብ ድርጀት ተጨማሪ የአውሮፕላን ድጋፍ ማድረጉ የመከላከል ስራውን ይበልጥ ውጤታማ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

በቀጣይም ተጨማሪ አውሮፕላኖች ወደ ስራ በማስገባት ሰፊ የመከላከል ስራ ለመስራት እቅድ ተይዞ እየተሰራ ይገኛል ማለታቸውን የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል።
(ኢ.ፕ.ድ)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top