Connect with us

ከ51 ሺህ በላይ ሕዝብ ዕጣ የወጣለት ሕዝብ ቤቱን ሳይረከብ አንድ ዓመት ደፈነ

ከ51 ሺህ በላይ ሕዝብ ዕጣ የወጣለት ሕዝብ ቤቱን ሳይረከብ አንድ ዓመት ደፈነ

ህግና ስርዓት

ከ51 ሺህ በላይ ሕዝብ ዕጣ የወጣለት ሕዝብ ቤቱን ሳይረከብ አንድ ዓመት ደፈነ

ከ51 ሺህ በላይ ሕዝብ ዕጣ የወጣለት ሕዝብ ቤቱን ሳይረከብ አንድ ዓመት ደፈነ
(ጫሊ በላይነህ)

ልክ የዛሬ ዓመት የአዲስአበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ በተገኙበት የ 13ኛው ዙር ኮንደምኒየም ዕጣ በይፋ ወጣ፡፡ የዕጣውን መውጣት ተከትሎ በእነጀዋር መሐመድ የሚመራ ጥቂት ወጣቶች የኦሮሚያ ገበሬ ተፈናቅሎ አንድም ሰው ወደእነዚህ ቤቶች አይገባም የሚል ቅስቀሳ እና ሰልፍ አካሄዱ፡፡ ይህን ተከትሎ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ተቃውሞውን የሚደግፍ መግለጫ በማውጣት ቤቶችን የማስተላለፍ ስራው እንዲዘገይ ጠየቀ፡፡ የዶ/ር ዐብይ አሕመድ አስተዳደር ጉዳዩን የሚያጠናና የመፍትሔ ሀሳብ የሚያቀርብ ኮምቴ አዋቀረ፡፡ እነሆ ይኸ ከሆነ አንድ ዓመት ደፈነ፡፡ ግን አሁንም ቄሱም ዝም ፤መጽሐፉም ዝም ማለቱ ሕዝብ በመንግሥት ላይ ያልተገባ ጥርጣሬ እንዲያነሳ ምክንያት እየሆነ ነው፡፡ ያለፈው ዓመት በዚህ ወቅት የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ባለዕድል የሆነው ከ51 ሺ በላይ ሕዝብ ከዛሬ ነገ ቤቴን እረከባለሁ በሚል ተስፋ እንደቆዘመ አንድ ዓመቱን ደፈነ፡፡

ይህ ክስተት በመንግሥት ላይ ሙሉ እምነት ኖሮአቸው አንድ ቀን ቤት እናገኝ ይሆናል በሚል ተስፋ የሚቆጥቡ በርካታ ዜጎችን ተስፋ አስቆርጧል፡፡ ጥቂት የማይባሉትም ከዕለት ጉርስ ቀንሰው የሚቆጥቡትን ለማቋረጥ ተገደዋል፡፡ ብዙዎች በመንግሥት ልፍስፍስ አቋም አዝነዋል፡፡

ከምንም በላይ በእኔ ዕይታ ታታሪው፣ ጎበዙ የከተማችን ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ምንም ማድረግ አለመቻላቸው ብቻ ሳይሆን ለዚህ ሕዝብ ተስፋ እንኳን መስጠት አለመቻላቸው የሚያሳዝን ሆኗል፡፡ በተለይ 40 በ60 ቤቶች ዕጣ የደረሳቸው ወገኖች ተገቢውን የቤት ማስተላለፍ ውል ቢፈጽሙም ቤታቸውን መረከብ አልቻሉም፡፡ የ20 በ80 ወይንም ኮንደሚኒየም ዕድለኞች ደግሞ ጨርሶ ቤት ለመረከብ የሚያስችል ውል አለመፈራረማቸው ሥጋታቸውን እንዲጨምር፣ ላልተፈለገ ወሬና አሉባልታ እንዲጋለጡም አድርጓል፡፡

ኢንጂነር ታለከ ኡማ ይኸን ተግዳሮት እንዴት ይፈቱት ይሆን?

ለማንኛውም የኮንደሚኒየም ዕጣ ተስፈኛ ዜጎች ሆይ እንኳን ዕጣ እንደደረሳችሁ ላወቃችሁበት አንደኛ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ እያልኩኝ አምና በዚህ ሰዓት ፋና ዘግቦት የነበረው ዜና ለትውስታ ያህል አያይዥዋለሁ፡፡

***

በአዲስ አበባ 51 ሺህ 229 የጋራ መኖሪያ ቤቶች (ኮንዶሚኒየም ቤቶች) ዕጣ ማውጣት ሥነ ስርዓት ተካሄደ

ዕጣ ከወጣባቸው ቤቶች ውስጥም 32 ሺህ 653 ቤቶች የ20/80 ቤቶች ሲሆኑ፥ ቀሪዎቹ 18 ሺህ 576 ደግሞ የ40/60 ቤቶች ናቸው። በዚህም መሠረት የ20/80 ፕሮግራም ኮንዶሚኒየም ቤቶች ውስጥ 1 ሺህ 248 ስቲዲዮ፣ 18 ሺህ 823 ባለ አንድ መኝታ፣ 7 ሺህ 127 ባለ ሁለት መኝታ እና 5 ሺህ 455 ቤቶች ደግሞ ባለ ሦስት መኝታ ክፍሎች ናቸው። በእነዚህ የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውስጥ የሚካተቱት በ1997 ዓ.ም ተመዝግበው በ2005 ዓ.ም በነባር መደብ የተመዘገቡና በ2005 ዓ.ም የአዲስ ባለ ሦስት መኝታ ክፍል ተመዝጋቢዎች ናቸው።

በዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ እንደተናገሩት፥ በግንባታ ሂደት ሁሉም ተጠቃሚ እንደሚሆን ቢታሰብም በጥንቃቄ ጉድለት ለጉዳትና ማኅበራዊ ቀውስ የተዳረጉ የህብረተሰብ ክፍሎች አሉ። ኢንጅነር ታከለ ልማት በጋራ ተጠቃሚነት ካልተጀመረ ተጎጅና ተጠቃሚን የሚፈጥርም ነው ብለዋል። በተለይ ለቤቶች ግንባታ ሲባል ከእርሻ ቦታቸው የለቀቁ አርሶ አደሮችና የአርሶ አደር ልጆች የሁላችንም ህመም ነው ብለዋል። በዚህም የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔና የቤቶች አሰተዳደር ቦርድ አርሶ አደሮችና የአርሶ አደር ልጆች ያለ ዕጣ እንዲሰጣቸው መወሰኑን ይፋ አድርገዋል።

ኢንጂነር ታከለ በቀጣይም የቤት ልማትን ከአርሶ አደሩ ተጠቃሚነት ጋር ለማስኬድ ትኩረት በማድረግ ይሠራል ነው ያሉት። በቤት ልማቱ የመንግስትን ተሳትፎ በመቀነስ የግሉንና የባለሀብቱን ተሳትፎ የማሳደግ ሥራ እንደሚከናወንም ጠቁመዋል። ከንቲባው በዘርፉ የመንግስትና የባላሀብቶችን ግንኙነትን ለማጠናከር በትኩረት ለመንቀሳቀስ ኮሚቴ መዋቀሩን ነው ያስታወቁት።

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር አቶ ዣንጥራር አባይ በበኩላቸው፥ መንግስት በቤት ልማት ዘርፍ የሚታየውን ችግር ለመቅረፍ በርካታ ሥራዎች ሲያከናውን መቆየቱን የተናገሩ ሲሆን፥ በዚህ ወጤቶች መመዝገባቸውን አንስተዋል። በቤት ልማት ዘርፉ የፍላጎቱን ያህል ባይሠራም የተሻለ ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

አቶ ዣንጥራር በኢትዮጵያ ያለው የቤት ልማት ዘርፍ ህዝቡን የቤት ባለቤት ከማድረግ ባለፈ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል የፈጠረ መሆኑን አስታውቀዋል። ባለፉት 13 ዓመታት በአዲስ አበበና በመላ ሀገሪቱ ከ385 ሺህ በላይ ቤቶች እንደተገነቡና በግንባታ ላይ እንደሚገኙ የገለፁ ሲሆን፥ በዚህም 1 ሚሊየን ለሚጠጉ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር እንደተቻለ ተናግረዋል።

በተለያዩ ወገኖች በተደረገ ጥናት መሠረት ካለው የቤት ፍላጎት አንፃር ከ2007 እስከ 2017 ዓመተ ምኅረት ባለው ጊዜ ውስጥ 471 ሺህ ቤቶችን በየዓመቱ እየገነቡ ማቅረብ ይገባ ነበር። ሆኖም መንግስት በፋይናንስ እና በግንባታ ፕሮጀክት የማስፈፀም አቅም ባለበት ክፍተት ምክንያት ይህን ማድረግ እንዳልተቻለ በመጠቆም በቀጣይ የግሉን ዘርፍ በማሳተፍ ፍላጎቱን ለማሟላት እንደሚሠራ ነው አቶ ዣንጥራር በንግግራቸው ላይ ያነሱት።((የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም.)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top