Connect with us

በከተሞች ጎዳና አደባባዮች ላይ የኦነግ ባንዲራ በሚውለበለብባት ሀገር ለምን የሀገርህን ሰንደቅ ያዝክ ብለው ጠብ የሚያነሱ የጸጥታ አካላት …

በከተሞች ጎዳና አደባባዮች ላይ የኦነግ ባንዲራ በሚውለበለብባት ሀገር ለምን የሀገርህን ሰንደቅ ያዝክ ብለው ጠብ የሚያነሱ የጸጥታ አካላት
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

በከተሞች ጎዳና አደባባዮች ላይ የኦነግ ባንዲራ በሚውለበለብባት ሀገር ለምን የሀገርህን ሰንደቅ ያዝክ ብለው ጠብ የሚያነሱ የጸጥታ አካላት …

በከተሞች ጎዳና አደባባዮች ላይ የኦነግ ባንዲራ በሚውለበለብባት ሀገር ለምን የሀገርህን ሰንደቅ ያዝክ ብለው ጠብ የሚያነሱ የጸጥታ አካላት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ስውር ጠላቶች ናቸው፡፡ አድዋ አከባበር ላይም ይሄን አይተናል፤
****
ከስናፍቅሽ አዲስ
አንዳንድ የጸጥታ ሃይሎች ዓላማቸውን ለማሳካት እየሰሩ ነው፡፡ ጠቅላዮን ለማክሸፍ ህዝቡን አስቀይመው የሚል ስሌት ውስጥ የገቡ ይመስለኛል፡፡ ዛሬም የባንዲራ ጉዳይ ዶክተር አብይን ከሚመሩት ጋር ቆርሾ ውስጥ እንዲከት እየሰሩ ያሉ የጸጥታ አስከባሪዎች እየታዩ ነው፡፡

ጥምቀትና መስቀል ከቀሚስ ላይ ሳይቀር አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ ያለበትን ምልክት ሲነቅሉ የታዮት የጸጥታ ሃይሎች ናቸው፡፡ በዘንድሮው አድዋ ድል በዓል ባንዲራ የሚመስል ነገር የያዘም የለበሰም ለማስወለቅ ሲሟገቱ የነበሩ ሃይሎችን ታዝበናል፡፡ ካራ ማራ በድላችን ሀውልት ሲከበርም ተመሳሳይ ሀሳብ ያላቸው የጸጥታ ሃይሎች ነበሩ፤ ዓላማው ዶክተሩን እሚያማርና እሚጠራጠር ህዝብ ማብዛት ነው፡፡

ዛሬ በሻሸመኔ አደባባይ የኦነግ ባንዲራ በይፋ የሚውለበለብባት ሀገር ህግና ሥርዓት ላስከብር ነው ብሎ የአባቶቻችንን ሰንደቅ አልመልከት ካለን ጠቡ ከእኛ ሳይሆን ከሀገር መሪው ጭምር እንደሆነ ቢገባንም መፍትሔ ግን አላገኘም፡፡ የፀጥታ ሃይሎቹ ምን ፈልገው እንደሆነ መገመቱ ቀላል ነው፡፡ ጠቅላዮን ከሰው ልብ ጠቅልሎ ለማስወጣት፤

በአድዋ ድል በዓል የአሜሪካንን ሻሽ ያደረገ ሰው እንደ ልቡ ገብቶ አባቶች አደዋ ይዘውት የዘመቱትን ባንዲራ የያዘ ሰው አውልቅ ማለት ትርጉም ፈላጊ አያሻውም፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጸጥታ መዋቅራቸውን ደጋግመው መፈተሽ አለባቸው፡፡ የሳቸውን ቲሸርት ጭምር የለበሰ ሰው በግልምጫ የሚያነሱ ከተመቻቸው የሚጎሽሙ የጸጥታ ሃይሎች ዛሬም አሉ፡፡

የባንዲራ ጉዳይ ይሄንን ያህል እንዲከር የተፈለገው አክራሪ የነበሩ ሰዎች ዛሬም ያን ጨካኝ በትራቸውን ይዘው አደባባይ ስለቆሙ ነው፡፡ የሀገር ይፋዊ ባንዲራ አውርዶ የራሱን ያውለበለበ ሃይል ባለበት ሀገር ላይ ከሀገር ልብስ ቀለም ልቁረጥ የሚል ወይም ስካርፕ የሚነጥቅ ወይም ኮንሰርት በር ላይ ቆሞ ይሄንን ባንዲራ አልመልከት የሚል ወገን በየስብሰባ ስፍራው እየመጣ ህዝብና መንግስት ካልተቀያየመ የሚል እስኪመስል ዛሬም ትንኮሳውን ቀጥሏል፡፡ ትናንት የእስክንድር ነጋ ባንዲራ መያዝ ያስኮረፈው የጸጥታ ሃይል እየተቀረጸ ያሳየው ተግባር በቂ ምልክት ይመስለኛልና የሚመለከተው አካል አንድ ይበል፤

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top