Connect with us

ኦሮምያ ሚዲያ ኔት ወርክ የቃለ መጠይቅ ግብዣ ማድረጉ መርሕ የተከተለ አለመሆኑን ጴጥሮሳውያን ገለጠ

ኦሮምያ ሚዲያ ኔት ወርክ የቃለ መጠይቅ ግብዣ ማድረጉ መርሕ የተከተለ አለመሆኑን ጴጥሮሳውያን ገለጠ

ህግና ስርዓት

ኦሮምያ ሚዲያ ኔት ወርክ የቃለ መጠይቅ ግብዣ ማድረጉ መርሕ የተከተለ አለመሆኑን ጴጥሮሳውያን ገለጠ

ኦሮምያ ሚዲያ ኔት ወርክ የቃለ መጠይቅ ግብዣ ማድረጉ መርሕ የተከተለ አለመሆኑን ጴጥሮሳውያን ገለጠ

ኦሮምያ ሚዲያ ኔት ወርክ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ እውነትነቱ ያልተረጋገጠ፣ ክብርና ልዕልናን የሚጋፋ መርሐግብር በመሥራቱ የኢትዮጵያ ብሮድ ካስት ባለሥልጣን ቤተ ክርስቲያንን ይቅርታ እንዲትጠይቅና በተመሳሳይና እኩል በሆነ የአየር ሰዓት የቤተ ክርስቲያኗን ምላሽ እንዲያስተናግድ የሰጠውን ትእዛዝ ወደ ጎን ብሎ በአቋራጭ ጴጥሮሳውያን የቤተ ክርስቲያን ክብርና መብት አስጠባቂ ኅብረትን ለቃለ ምልልስ መጥራቱ መርሕ ያልተከተለ በመሆኑ እንደማይቀበለው ኅብረቱ ገለጠ።

የእነጀዋር ኦኤምኤን ምን አጥፍቶ ተከሰሰ?
(ጫሊ በላይነህ)

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ለአሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ (OMN) የጻፈው አራት ገጽ ያዘለ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ተመለከትኩት፡፡ ቀድሞውኑ ባለሥልጣኑ የኢትዮጵያ ዜግነት የሌለው ግለሰብ በብሮድካስት ሥራ ሲሰማራ ዝም ብሎ መመልከቱ ትልቅ ስህተት የነበረ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ እጅግ ዘግይቶም ቢሆን ተገቢውን እርምጃ ወደመውሰድ መሸጋገሩ ይበል የሚያሰኝ ጅምር ነው፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጴጥሮሳውያን የቤተክርስቲያን ክብር እና መብት አስጠባቂ ኅብረት በኦኤምኤን ላይ ለባለሥልጣኑ የጻፈውን የጻፈው ደብዳቤ መሰረት በማድረግ ባለሥልጣኑ ኦኤምኤን አስተያየቱን ጭር እንዲሰጥ በማድረግ የውሳኔ ሃሳቡን በትላንትናው ዕለት በድብዳቤ ገልጿል፡፡ ደብዳቤው ምን አዲስ ሃሳብ ይዟል? አንኳር ነጥቦችን እዳስሳለሁ፡፡

ኦ ኤም ኤን ላይ ቅሬታ የቀረበው ጥር 9 ቀን 2012 ዓ.ም በኦሮምኛ ቋንቋ በጣቢያው በተሰራጨው በፕሮፌሰር መረራ ጉዲና የሚመራው ኦፌኮ በገብረጉራቻና በፍቼ ባከናወነው የምርጫ ቅስቀሳ የሚመስል ሕዝባዊ ጉባዔ ላይ አቶ ኃይለሚካኤል ታደሰ የተባሉ ግለሰብ ያደረጉት ንግግር ይዘት ነው፡፡ ባለሥልጣኑ ቅሬታውን (ክሱን) ከብሮድካስት አዋጅ 533/99 አንጻር በመመርመር የሚከተሉትን ጉድለቶች ማግኘቱን ይፋ አድርጓል፡፡

ኦኤምኤን ያልተረጋገጡና ምንጫቸው ያልታወቁ መረጃዎችን ከማቅረብ አኳያ፣ እንዲሁም የሌሎችን እምነት በማንኳሰስ፣ በሕዝቦች መካከል የእርስ በእርስ ግጭት የሚቀሰቀስ፣በሐሰት የሚወነጅል ንግግርን በማስተላለፍ ተከሷል፡፡ በጣቢያው የተላለፈው አስደንጋጭና አስነዋሪ የአቶ ኃይለሚካኤል ታደሰ ንግግር የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፡፡

“እናንተ የኦሮሞ ወጣቶች በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ እንግዶች ሆናችል፡፡ ለምንድነው እንግዶች የሆናችሁት? ዶ/ር ብርሃኑ ነጋን መስቀል አሳልማ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲናን የምታገል ቤ/ክ አንፈልግም..በሃይማኖት የምትከፋፍለን ቤ/ክ አንፈልግም.. ኦሮሞን በጎሳ የምትከፋፍል ቤ/ክ አንፈልግም…”በተክርስቲያንዋ የፊውዳሎች ኤምባሲ ሆናለች…….የፖለቲካ ኤምባሲ መፍረስ አለበት፣ የፊውዳሎች የፖለቲካ ኤምባሲ መፍረስ አለበት፣ የቀድሞ ሰዎች የፖለቲካ ኤምባሲ መፍረስ አለበት….ቤተክርስቲያንን ሰብራችሁ ግቡ እና ከእጃቸው ተቀብላችሁ እጃችሁ አስገቡ፣ኦሮሞን ነጻ እናወጣለን፣ ደብረሊባኖስ የእናንተ ነው፡፡ ከአሁን በሃላ ደብረሊባኖስ ላይ የምታዙት እናንተ ናችሁ፣ እኛ ሰላሌ ላይ ቤተክርስቲያንን ነጻ ማውጣት አለብን፡፡”የሚል ይዘት ያላቸው ናቸው፡፡”

ከሁሉ የሚገርመው ይህ አጸያፊ ንግግር የተነገረው የፖለቲካ ሳይንቲስት ነኝ ባዩ አቶ ጀዋር መሐመድ በተገኘበት መድረክ መሆኑ እና አቶ ጀዋር ሲያስተዳድረው በኖረው ኦኤም ኤን ቲቪ ላይ የቀረበ መሆኑ ነው፡፡

ምናልባት የሰውየው ንግግር አስቀድሞ የታቀደ ስለመሆኑ ቅንጅቱ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡

ያም ሆነ ይህ ኦኤምኤን ለፈጸመው የሕግ ጥሰት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሰ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅ፣ በሕጉ መሠረት በቀረቡት ይዘቶች ተመጣጣኝ የሆነ የቤተክርስቲያንዋ መልስ እንዲያስተናገድ በባለሥልጣኑ ታዟል፡፡ በተጨማሪም በቀጣይ መሰል ስህተት እንዳይደግም ማስጠንቀቂያ ተቀብሏል፡፡ በዚህ የባለሥልጣኑ ውሳኔ መሠረት ኦኤምኤን የታዘዘውን በመፈጸም ስህተቱን ያርማል ወይ የሚለውን በቅርብ አብረን የምናየው ይሆናል፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top