Connect with us

ሄይኒከን ኢትዮጵያ ማህበረሰብ አቀፍ ፕሮጀክቶችን ደገፈ

ሄይኒከን ኢትዮጵያ ማህበረሰብ አቀፍ ፕሮጀክቶችን ደገፈ

ኢኮኖሚ

ሄይኒከን ኢትዮጵያ ማህበረሰብ አቀፍ ፕሮጀክቶችን ደገፈ

ሄይኒከን ኢትዮጵያ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ከ35 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የተለያዩ ለማህበረሰብ ተኮር ፕሮጀክቶች ድጋፍ አደረገ፡፡

ማክሰኞ የካቲት 17 ቀን 2012 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ ከተማ ለሚገኙ ወጣቶች ለመደገፍ የሚውል ከ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ የወጣበት የወፍጮ ቤት ከአራት የእህል ወፍጮዎች ጋር ሰርቶ በይፋ አስረክቧል፡፡ በርክክቡ ሥነሥርዓት ላይ የተገኙት የሻሸመኔ ከተማ ከንቲባ አቶ ተማም ሁሴን ሄይኒከን ኢትዮጵያ ያደረገው ድጋፍ ወጣቶችን የሥራ አጥነት ለመቅረፍ አስተዳደሩ እያደረገ ላለው መጠነ ሰፊ ጥረት ትልቅ እና ትርጉም ያለው እገዛ ነው በማለት ለተደረገው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡

የአካባቢው ወጣቶች የሄይኒከን ቢራ ድጋፍ ወጣቶች ከሥራ አጥነት ወደሠራተኝነት እንዲሸጋገሩ፣ ሌሎችም እንዲነቃቁ የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል ሄይኒከን ኢትዮጵያ ከወርልድ ቪዥን ጋር በመተባበር ከ120 ሺ በላይ ሕዝብ ሊጠቅም የሚችል የአካባቢ ጥበቃና አያያዝ ላይ ያተኮረ የቡርቃ ኢንሼቲቭ የተሰኘ የሶስት ዓመት ፕሮጀክት ቦሌ አካባቢ በሚገኘው ቤስት ዌስት ሆቴል ሐሙስ የካቲት 19 ቀን 2012 ዓ.ም ይፋ ሆኗል፡፡ በዕለቱ የሁለቱም ወገኖች የስምምነት ፊርማ ተከናውኗል፡፡ የአካባቢ ጥበቃን በማሻሻል የሕዝቡን የንጹህ ውሃ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ፕሮግራሙ የላቀ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡ ለዚህ ፕሮግራም ሄይኒከን ኢትዮጵያ 30 ሚሊየን ብር ወጪ እንደሚሸፍን ታውቋል፡፡

በተጨማሪም ዓርብ የካቲት 20 ቀን 2012 ዓ.ም ሄይኒከን ኢትዮጵያ በአዲስአበባ ከተማ በአማኑኤል የአዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ ያሰራውን የህክምና መስጫ ክፍሎች አስረክቧል፡፡

ከተቋቋመ ሰማንያ ሁለት ዓመታትን ያስቆጠረው የቅዱስ አማኑኤል የአዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የእናቶችና ህፃናት ጤና አገልግሎት እንዲሁም የሥነ አዕምሮ ድንገተኛ ህክምና መስጫ ህንፃ በ4 ነጥብ 2 ሚ ገንብቶ በዛሬው ዕለት አስረክቧል፡፡

በ520 ካ.ሜ ላይ ያረፈው ህንፃው 23 ክፍሎች ያሉት ሲሆን የሥነ አዕምሮ ህክምና፣ የእናቶችና ህፃናት ጤና ምርመራ አገልግሎትን እንደሚሰጥ ተነግሯል፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top