Connect with us

የእነክርስቲያን ታደለ እና ኤርሚያስ አመልጋ ክስ ተቋርጧል

የእነክርስቲያን ታደለ እና ኤርሚያስ አመልጋ ክስ ተቋርጧል
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

የእነክርስቲያን ታደለ እና ኤርሚያስ አመልጋ ክስ ተቋርጧል

የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር ብ/ጀነራል ክንፈ ዳኘው ክሳቸው አለመቋረጡ ተሰምቷል

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ክርስቲያን ታደለ፣ ኤርሚያስ አመልጋ፣ ኮ/ል ቢኒያም ተወልደ ክሳቸው ተቋርጦ በዛሬው ዕለት ከሚፈቱት እስረኞች መካከል ሆነዋል።

አቶ ክርስቲያን በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሐምሌ 4 ቀን 2011 ዓ.ም. በፌዴራል ፖሊስ ታስረው የሚገኙ የአብን አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎችን ፒያሳ አካባቢ በሚገኘው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እስር ቤት ጠይቀው ሲመለሱ ነበር።

ኤርሚያስ ክሱ ተቋርጦ ከእስር እንዲፈታ ከተወሰኑት መካከል ሲሆን ከ አንድ አመት በላይ ታስሮ ቆይቷል።

ክሳቸው ከተቋረጠላቸው 63 ግለሰቦች መካከል ረ/ፕሮፌሰር ተሰማ ኤልያስ፣ አቶ ሳሙኤል በላይነህ፣ አቶ አዲስ ቃሚሶ እና የአለም ገነት ቆርቆሮ ፋብሪካ እና የሪቬራ ሆቴል ባለቤት አቶ አለም ፍጹም እንደሚገኙበት ምንጫችን ጠቁመዋል።

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top