Connect with us

በብሔራዊ ፓርኮች የሚገጥሙ የእሳት ቃጠሎዎችን መከላከል የሚያስችል የአሰልጣኞች ስልጠና ዛሬ ይጠናቀቃል

በብሔራዊ ፓርኮች የሚገጥሙ የእሳት ቃጠሎዎችን መከላከል የሚያስችል የአሰልጣኞች ስልጠና ዛሬ ይጠናቀቃል

ዜና

በብሔራዊ ፓርኮች የሚገጥሙ የእሳት ቃጠሎዎችን መከላከል የሚያስችል የአሰልጣኞች ስልጠና ዛሬ ይጠናቀቃል

በተደጋጋሚ በብሔራዊ ፓርኮች ላይ የሚከሰተውን የእሳት ቃጠሎ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል የአሰልጣኞች ስልጠና በስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ሲሰጥ ቆይቷል፡፡

ዛሬ የተጠናቀቀው ስልጠና ባለፉትን አስራ ሁለት ቀናት የተካሄደ ሲሆን በዋናነትም ብሔራዊ ፓርኮቻችን የሚገጥማቸውን የእሳት አደጋዎች አስቀድሞ ለመከላከል፣ እሳት አደጋዎቹ ሲደርሱ ደግሞ በቀላሉ ለመቆጣጠር የሚያስችሉ እድሎች የሚፈጥር ስልጠና ነው፡፡

የስልጠናው አስተባባሪና በዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን የፓርኮች ጥበቃና ልማት ዳይሮክተሬት ባለሙያ የሆኑት አቶ አስቻለው ጸጋዬ ለድሬ ቲዩብ ዘጋቢ እንደገለጹት 60 የሚደርሱ ሰልጣኞች ስልጠናውን የተሳተፉ ሲሆን ከእነኚህ ውስጥም ከባሌ ተራሮችና ከስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርኮች ከእያንዳንዳቸው ሃያ ሃያ ሰልጣኞችን ጨምሮ በፌዴራል ስር የሚተዳደሩት ብሔራዊ ፓርኮችና የዱር እንስሳት መጠለያዎች የሚገኙ የስራ ሃላፊዎች፣ የቦረና ሳይንት፣ የጎደቤ፣ የጨበራ ጩርጩራና የማጎ ብሔራዊ ፓርኮች በስልጠናው ታሳታፊ ሆነዋል፡፡

ከትናንት በስቲያ በስልጠናው ላይ ተገኝተው ለሰልጣኞች ንግግር ያደረጉት የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጅራ እንደገለፁት የስልጠናው ዓላማ በተደጋጋሚ የሚከሰተውን የብሔራዊ ፓርኮች የእሳት አደጋ ለመከላከል የሚቻልበትን እውቀትና ክህሎት ለመስጠት ያቀደ መኾኑን ገልፀው ሰልጣኞቹ ወደየመጡበት የብሔራዊ ፓርኮችና ዱር እንስሳት መጠለያዎች ሲሄዱ ከስልጠናው ያገኙትን እውቀት ለሌሎች እንዲያካፍሉ ማሳሰባቸውን የባለ ስልጣን መስሪያ ቤቱ የፌስ ቡክ ገፅ አስፍሯል።

ከወንዶ ገነት ዩኒቨርሲቲ፣ ከደቡብ አፍሪካ፣ ከብሔራዊ አደጋ መከላከል ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በተውጣጡ ባለሙያዎች ሲሰጥ የቆየው ይህ ስልጠና የሀገር ውስጥ የውጪ ባለሙያዎች በተግባርና በንድፈ ሀሳብ በአስልጣኝነት የተሳተፉበት እንደሆነ አቶ አስቻው ገልጸዋል፡፡

ባሳለፍነው በጋ ወቅት ብሔራዊ ፓርኮቻችን ተደጋጋሚ የእሳት ቃጠሎ ገጥሟቸው እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top