Connect with us

የአማራ ክልል ምክር ቤት ዶ/ር ፋንታ ማንደፍሮ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አድርጎ ሾመ

የአማራ ክልል ምክር ቤት ዶ/ር ፋንታ ማንደፍሮ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አድርጎ ሾመ
Photo: Facebook

ዜና

የአማራ ክልል ምክር ቤት ዶ/ር ፋንታ ማንደፍሮ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አድርጎ ሾመ

የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን አስቸኳይ ጉባኤ ላይ ሰፊ ክርክር ከተደረገ በኃላ ምክር ቤቱ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እንዲሆኑ የቀረበውን የፋንታ ማንደፍሮ/ዶ/ር/ን ሹመት አፅድቋል፡፡

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ የዕጩ ተሿማዎችን ለምክር ቤቱ አባላት ሲያቀርቡ እንዳሉት ወቅቱን የዋጀ በዕውቀት ላይ የተመሠረተ አመራር ለመስጠትና ኃላፊነትን በአግባቡ ለመወጣት የሚጠይቅ ወቅት ላይ በመሆናቸው ሹመቱ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ላቀ አያሌው፣ የአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ቧያለው፣ በምክትል ርእሰ መስተዳድር ደረጃ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ መላኩ አለበል እና የከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋንታ ደጀን በፌዴራል መንግሥት ደረጃ ኃላፊነት ስለተሰጣቸው በምትካቸው አዳዲስ ሹመት መስጠት እንዳስፈለገ ርእሰ መስተዳድሩ አስገንዝበዋል፡፡

የክልሉ ምክር ቤት አባላት በአንጻሩ ክልሉ ላይ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች የነበሩት አመራሮች ወደ ፌደራል መሄዳቸው ክልሉ በዚህ ፈታኝ ወቅት ይጎደዋል ሲሉ ተከራክረዋል፡፡

በመሆኑም አመራሮቹ ክልሉ ላይ የቆዩ በመሆናቸው ባሉበት ቦታ ሆነው ቢሰሩ ክልሉ ያሉበትን ችግሮች ለመሻገር ይጠቅሙታል ፣ በአንጸሩ ለፌደራል ሹመት ሌሎችን ማቅረብ ይቻላል ብለው ተከራክረዋል ፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በበኩላቸው ምክር ቤቱ የፓርቲና መንግስታዊን ስራ ለያይቶ እንዲመለከትና ለክልሉ መንግስት የስራ ኃላነፊቶች የታጩ ግለሰቦች በአግባቡ እንደሚሰሩ በማመን የቀረቡ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡በተጨማም ወደ ፌደራል ለተለያዩ የስራ ኃላፊነቶች የታጩ አመራሮች የክልሉን ጥቅም በፌደራል ደረጃ ለማስከበር ታስቦ የተደረገ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

በመሆኑም ፋንታ ማንደፍሮ/ዶ/ር/ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩትን አቶ ላቀ አያሌውን በመተካት ፋንታ ደጀን/ዶ/ር/ን ምክትል ርእሰ መስተዳድር እንዲሆኑ የቀረበውን ሹመት በአብላጫ ድምፅ በ3 ተቃውሞና በ44 ድምፀ ተዓቅቦ ምክር ቤቱ አጽድቆታል፡፡(ኢቲቪ)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top