Connect with us

ጌታቸው አሰፋ ለዕውቅና የምስክር ወረቀት ወደመድረኩ ቢጠሩም “አቤት” የሚል ሰው ጠፋ

ጌታቸው አሰፋ ለዕውቅና የምስክር ወረቀት ወደመድረኩ ቢጠሩም "አቤት" የሚል ሰው ጠፋ
Photo: VOA

ህግና ስርዓት

ጌታቸው አሰፋ ለዕውቅና የምስክር ወረቀት ወደመድረኩ ቢጠሩም “አቤት” የሚል ሰው ጠፋ

የህወሓት 45ኛ ዓመት የምስረታ “የካቲት 11” በዓል ምክንያት በማድረግም ለነባር ታጋዮች ዕውቅና ተሰጥቷል።

በትጥቅ ትግሉ ጊዜ ለነበሩ የህወሓት ታጋዮች የእውቅና መርሃ ግብር በትለንትነው ዕለት አዘጋጅቶ ነበር። ፓርቲውን ለመሰረቱ፣ ለስራ አስፈፃሚና በማዕከላይ ኮሚቴዎች እንዲሁም የቁጥጥር ኮሚሽን አመራር ለነበሩና ላሉ ታጋዮች እውቅና ሰጥቷል።

ትላንት በነበረው የእውቅና መስጠት መርሃ ግብር አቶ ስዩም መስፍን፣ አቶ ስዬ አብርሃ፣ ጀነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤን ጨምሮ የፓርቲው ነባር አመራሮች ተገኝተው ነበር።

በመርሃ ግብሩ ላይ በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ እንደሚፈልጉ በተደጋጋሚ የሚገለፀው የቀድሞው የመረጃና ደህንነት ኃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋ ለእውቅና የምስክር ወረቀት ወደመድረኩ ተጠርተው የነበረ ቢሆንም ቀርበው ሲወስዱ አልታዩም።

ህወሓት እስካሁን ድረስ ለ91 ሺ ታጋዮች የዕውቅና ምስክር ወረቀት ሰጥቷል።

በተያያዘ ዜና 45ኛው ዓመት የየካቲት 11 በዓል ምክንያት በማድረግ በመቐለ ከተማ ደማቅ የጎዳና ትርኢት ተካሂዷል።

ህወሓት የተመሰረተበት 45ኛው ዓመት የካቲት 11 በዓል ምክንያት በማድረግ የካቲት 9 ቀን 2012 ዓ/ም በመቐለ ከተማ ደማቅ የጎዳና ትርኢት የተካሄደው።

በህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል እና ምክትል ሊቀመንበር ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረ/ሔር የተከፈተው በመቐለ እየተካሄደ ያለው የጎዳና ላይ ትርኢት የትግራይ ህዝብ ያካሄደው የትጥቅ ትግል ዓላማዎችና የተገኙ ውጤቶችን የሚያሳይ ነው።

በጎዳና ትርኢቱ ላይ 17 የመንግስት ቢሮዎች፣ 11 የግል ድርጅቶች፣ 7 የትእምት ድርጅቶች በድሞሩ 35 የመንግስትና የግል ድርጅቶች በ76 መኪኖች ላይ የተለያዩ የጎዳና ትርኢቶችን አቅርቧል። በጎዳና ትርኢቱ ላይ ከ1ሺህ ሰው በላይ ተሳትፏል።

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top