Connect with us

“የውሃ ያለህ” ወላድ እናቶች

"የውሃ ያለህ" ወላድ እናቶች
Photo: Facebook

ጤና

“የውሃ ያለህ” ወላድ እናቶች

በጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል አዳዲስ ማዋለጃ ክፍሎች ተዘጋጅተው አገልግሎት እየተሰጠ ቢሆንም በውሃ እጥረት ምክንያት ወላዶች ታጥበው ለመውጣት መቸገራው ተገለጸ። የትቁር አንበሳ ሆስፒታልም በተመሳሳይ ችግር በእናቶች ተተችቷል፡፡

የጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ታሪኩ ደሬሳ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ በሆስፒታሉ በወር ውስጥ ከአንድ ሺህ በላይ እናቶች ይወልዳሉ። በሆስፒታሉ የውሃ አቅርቦቱ በጣም የተቆራረጠ ነው።

ለማዋለጃ ክፍሎች ተብለው የተተከሉ የውሃ ማከማቻዎች ቢኖሩም በቀን አንድ ጊዜ ማታ የሚመጣው ውሃ ሊሞላቸው አልቻለም። በዚህም እናቶች ከወለዱ በኋላ ታጥበው ለመውጣት ተቸግረዋል።

እንደ ዶክተር ታሪኩ ገለፃ፤ ቀደም ብሎ እናቶች የሚወልዱበትን ስፍራ በመቀየር በአንድ ክፍል ውስጥ ሁሉንም ነገር እንዲጨርሱ የማድረግ አሰራር ተጀምሯል። ነገር ግን፤ በውሃ እጥረት ምክንያት ወላድ እናቶች ታጥበው መውጣት አለመቻላቸውን አዲስ ዘመን ጋዜጣ ዘግቧል፡፡

በተያያዘ ዜና የትቁር አንበሳ ሆስፒታልም በተመሳሳይ ሁኔታ የንጹህ ውሃ እና ንጡህ የመጸዳጃ ቤት ባለመኖሩ በክትትል ላይ ያሉ እናቶች መቸገራቸውን ገልጸዋል፡፡

በሆስፒታሉ ክትትል ከሚያደርጉ እናቶች አንድዋ ለድሬቲዩብ እንደተናገሩት ነፍሰጡር ሴት ቶሎ ቶሎ ሽንት የመምጣት ሁኔታ የተለመደ ነው፡፡ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እናቶች የእርግዝና ክትትል በሚያደርጉበት አካባቢ ለእናቶች ተብሎ የተዘጋጀ መጸዳጃ ቤት የለም፡፡ ራቅ ያሉት መጸዳጃ ቤቶች ንጽህና የጎደላቸው እና ውሃ የሌላቸው ናቸው፡፡ ሆስፒታሉ በቅጥር ግቢ ውስጥ የተለያዩ የማስፋፈፊያ ግንባታዎችን እያካሄደ ቢሆንም በተለይ ለመጸዳጃ ቤቶችን በመገንባትና በንጽህና በመያዝ ረገድ ትልቅ ክፍተት አለበት፡፡ በግሌ ሽንት ይመጣብኛል በሚል ውሃ እንኳን ለመጠጣት እሳቀቃለሁኝ ብለዋል፡፡

“አንድም እናት በመወሊድ ምክንያት መሞት የለባትም” የሚል መፈክር ከማሰማት በዘለለ የጤና ሚኒስቴር እና የአዲስአበባ ጤና ቢሮ ሆስፒታሎቹ ለእናቶች የሚረዱ የተሟላ የንጽህና መስጫ መሰረተ ልማቶች እንዲያሟሉ ሊሰሩ ይገባል ሲሉ ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡

(ምንጭ፡- ኢ.ፕ.ድ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top