Connect with us

ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል የፈፀሙት ተከሳሾች ተቀጡ

ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል የፈፀሙት ተከሳሾች ተቀጡ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል የፈፀሙት ተከሳሾች ተቀጡ

በህገ ወጥ መንገድ ኢትዮዽያዊያንን ወደ ዉጭ አገር በመላክ ወንጀል የፈፀሙ ሁለት ተከሳሾች ዐቃቤ ሕግ በመሰረተው 3 ክሶች በጽኑ እስራት እና በገንዘብ መቀጮ ተቀጡ፡፡

የክስ መዝገቡ እንደሚያስረዳው 1ኛ ተከሳሽ እንድሪስ አሊ እና 2ኛ ተከሳሽ እንድሪስ ሁሴን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32/1/ሀ/ እና 598/1/ ስር የተደነገገውን በመተላለፍ ኢትዮዽያዊያን ዜጎችን ለስራ ወደ ዉጭ አገር ለመላክ የሚያስችል ፍቃድ ሳይኖራቸው በ3ቱ ክስ ዝርዘር ስማቸው የተጠቀሱ በ1ኛ ክስ አቶ ሙሀመድ ሀሰን በ2ኛ ክስ ወ/ሪት መካ ሀስን እና በ3ኛ ክስ ወ/ሪት ሐውልት ሀሰን የተባሉ የግል ተበዳዮች ግንቦት 18 ቀን 2008 ዓ.ም ወደ ውጭ አገር እንደሚልካቸው በመግለጽ ለጊዜው ካልተያዘው ግብረአበራቸው ጋር በመሆን ከሚኖሩበት ከደቡብ ወሎ ዞን ወግዴ ወረዳ ወደ አዲስ አበባ እንዲመጡ እና ሳውዲ አረቢያ እንደሚልካቸው በመግለጽ ለስራ ማስጀመሪያ እያንዳንዳቸው 10,000 ብር፣ፓስፖርትና ፎቶ ግራፍ ከቀበሌ መታወቂያ ጋር ይዘው እንዲመጡ አድርገዋል፡፡

ተከሳሾች አዲስ አበባ ልዩ ቦታው አንዋር መስጊድ ፊት ለፊት 2ኛ ተከሳሽና ያልተያዘው ግብረአበሩ ከሆነው ደላላ ጋር በመሆን ተቀብለው እንደሚልኳቸው ቃል በመግባት ከእያንዳንዳቸው 10,000 ብር፣ፓስፖርትና ፎቶ ግራፍ ተቀብለው የጤና ምርመራ ከስደረጓቸው በኋላ በተናጠል ተጨማሪ ክፍያ 50,000 ብር የተቀበሉ ሲሆን በአጠቃላይ ከ3 የግል ተበዳዮች ከእያንዳንዳቸው 60,000 ብር በመቀበል በኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሳውዲ አረቢያ እንዲበሩ በማድረግ ሳውዲ አረቢያ አየር መንገድ ሲደርሱ በተናጠል የተያዙ ሲሆን የያዙት ዶክመንት ህገ ወጥ መሆኑ ተነግሯቸው ወደ አገራቸው የተመለሱ በመሆኑ ተከሳሾች በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈፀሙት በህገ ወጥ መንገድ ዜጎችን ለስራ ወደ ውጭ አገር መላክ ወንጀል ተከሰዋል፡፡

ለተከሳሾች ክሱ ደርሶ እንዲረዱት ከተደረገ በኋላ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሲጠየቁ የወንጀል ድርጊቱን ክደው የተከራከሩ በመሆኑ ዐቃቤ ሕግ እንደ ክሱ አቀራረብ የሚያስረዱ የሰዉ እና የሰነድ ማስረጃዎች ለፍርድ ቤቱ በማቅረብ እንዲሰሙለት ያደርገ ሲሆን ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን መርመሮ በ3ቱም ክሶች ጥፋተኛ ብሏቸዋል::

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 6ኛ ወንጀል ችሎት ታህሳስ 04 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት በ3ቱም ክሶች ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በ10 ዓመት ጽኑ እስራት እና 10 ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ሲል ወስኗል::(ምንጭ፡-የፌ/ጠ/ዐቃቤ ሕግ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top